ሙሽሮቹ "የጋብቻ ሥነ ሥርዓታችንን በሄሊኮፕተር ያካሄድነው ሞልቶን ተርፎን ሳይሆን የኢትዮጵያን የዕድገትና የለውጥ ሂደት ለኢትዮጵያውያንና ለመላው ዓለም ለማሳወቅ ነው" ብለዋል፡፡
"ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የምትታወቀው በረሃብና በድርቅ ነው" የሚሉት ሙሽሮቹ " በአሁኑ ወቅት ግን ኢትዮጵያ ዓለምን በሚያስደምም ሁኔታ እያደገች መሆኗንና የተለየ ገጽታ እንዳላት ለማሳወቅ በተለየ ሁኔታ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታችንን በሄሊኮፕተር ለማድረግ ችለናል" ነው የሚሉት ። የጋብቻ ሥነ ሥነ ሥርዓታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በሄሊኮፕተር ያካሄዱት አቶ ሙሉቀን ፋንታዬ ወይም በቅጽል ስሙ / ሉክ/ እና ወይዘሪት ወይንሸት ሙሉነህ ወይም በቅጽል ስሟ /ወይኒ/ ናቸው፡፡
ሉክ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ሙያዎች ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ወይኒ ደግሞ የአፄ ቴዎድሮስ አራተኛ የልጅ ልጅ ነች፡፡ በሊሞዚን መኪኖች በትልቅ ሆቴል ከሚካሄድ ቅልጥ ያለ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ያነሰ ወጪ እንዳወጡ የሚናገሩት ሙሽሮቹ ፥ በጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸው ላይ እንዲታደም የጠሩት የሰው ቁጥርም 150 ያህል ብቻ ነው፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ
No comments:
Post a Comment