Monday, August 17, 2020

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ የልህቀት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።

በአሜሪካ የሳቫና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ፕሮፌሰር የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው / ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ የሳይንስ፣ የሒሳብ እና የምሕንድስና የልህቀት ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

ዶ/ር ሙላቱ  ለማ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ በአፕላይድ ሂሳብ አግኝተዋል፡፡ ሀዋሳ እርሻ ኮሌጅ ለ 5 ዓመት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ለ 2 አመት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1988ዓ.ም የትምህርት እድል አግኝተው ወደ አሜሪካ - ኦሃዮ አመሩ፡፡ በዚያም እ.ኤ.አ በ1994 የሶስተኛ ዲግሪያቸውን/ዶክትሬታቸውን/ አግኝተዋል፡፡


በመምህርነት ሙያም ከ25 አመታት በላይ አገልግለዋል፡፡ በዚህ ያገልግሎት ቆይታቸውም ከ121 በላይ የጥናት እና ምርምር ውጤቶቻቸውን በልዩ ልዩ ጆርናሎች አሳትመዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመ “የሙላቱ ቁጥር” የሂሳብ ቀመርም ለዓለም አስተዋውቀዋል፡፡ 

በሳቫና ስቴት ዩኒቨርስቲ በሂሳብ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እየሰሩ የሚገኙት ዶ/ር ሙላቱ በ2013 “ጆርጂያ ፕሮፌሰር ኦፍ ዘ ይር” የሚል ሽልማትን አግኝተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ የሳይንስ፣ የሒሳብ እና የምሕንድስና የልህቀት ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። በአጠቃላይ እስካሁን በስራዎቻቸው ከ 8 በላይ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡


የአርሲ ሳጉሬ ተወላጁ ዶ/ር ሙላቱ ተወልደ በሙያቸው እና በስራቸው ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለኢትዮጵያ ኩራት ሆነዋል፡፡ ዶ/ር ሙላቱ ለሀገር እና ለህዝብ ኩራት በመሆንዎ እንኳን ደስ አልዎት ፣ ደስ አለን !!!

 

No comments:

Post a Comment