Monday, March 18, 2013


 የኬንያው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ክስ እንዲቋረጥ ግፊት ሊደረግ ነው


  የኬንያው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠበቆች አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የደንበኛቸውን ክስ እንዲያቋርጥ ግፊት ሊያደርጉ ነው።
   ከ5 ዓመት በፊት በተደረገው የኬንያ ምርጫ በተቀሰቀሰው ብጥብጥ ኴንያታ አሉበት በሚል ፍርድ ቤቱ በኢ- ስብዓዊ ድርጊት ከሷቸዋል።

     ክሱ ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግ አሊያም እንዲራዘም ነው የተመራጩ ፕሬዝዳንት ጠበቆች የጠየቁት። ባለፉት 10 ዓመታት ከከፈታቸው በርካታ ፋይሎች አንዱን ብቻ የረታው አለም አቀፉ ፍርድ ቤትም አወዛጋቢ እየሆነ መምጣቱን ነው የሮይተርስ ዘገባ የሚያሳየው ። ከኬንያታ ጋር የተከሰሱት የቀድሞው ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ፍራንሲስ ሙቶራ ፋይል መዘጋቱ የኬንያታን ክስ ውደቅ ለማድረግ ይረዳል እያሉ ነው ጠበቆቹ።

No comments:

Post a Comment