Tuesday, August 19, 2014

ሻደይ / አሸንዳ ጨዋታ....

                  

    በሰሜን ኢትዮጵያ ማለትም በትግራይ ፣ ዋግና ላስታ ከሚከናወኑ በርካታ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ጨዋታዎች መካከል እንደ ሸውላሌ ፣ ገና ጨዋታ ፣ አሸንድዬ / ሻደይ ፣ ሚሻሚሾ  እና ሆያ ሆዬ የመሳሰሉት በዓብይነት ይጠቀሳሉ፡፡ በነሐሴ ወር አጋማሽ ከፍልሰታ ፆም መፈታት ጋር ተያይዞ የሚከበረው የአሸንድዬ / ሻደይ በዓል ማራኪ እና ልዩ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ ይህ በዓል በላስታ አሸንድዬ ፣ በትግራይ አሸንዳ ፣ በዋግ ሻደይ ፣ በራያናቆቦ ሰለልበይ በመባል ተቀራራቢነት ባላቸው ስያሜ ይጠራል፡፡ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ወቅት ልጃገረዶች ከወገባቸው ላይ ሳር መሰል ቅጠል በማሰር ከቤት ቤት በመዘዋወር የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማሰማት የሚጫወቱት ጥንታዊ ፣ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡


  ሻደይ/አሸንዳ የሚለው ቃል ከሁለት ነገሮች ጋር እንደሚያያዝ የአካባቢው ቀደምት አዛውንቶች ያስረዳሉ፡፡ አንደኛው የድንግል ማሪያም እርገትን ምክንያት በማድረግ በከተማና በገጠር በልጃገረዶች እና በእናቶች አማካኝነት የሚደረግ ጨዋታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በዚህ ጨዋታ ወቅት በጨርቅ /በገመድ/ ተተብትቦ ወገብ ላይ የሚታጠቁት የኮባ ቅጠል ትልትል የሚመስልና ጫፈ ነጭ የሆነ ቅጠል መጠሪያ ነው ፡፡
  
   የሻደይ/አሸንዳ  ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ያስፈልገዋል፡፡ በመጀመሪያ ከሳምንት በፊት የቡድን አመሰራረት ምክክር ይደረጋል፡፡ ቡድኑ በተለያዩ የእድሜ ክልሎች የሚገኙ ልጃገረዶች እና እናቶችን የሚያካትት ነው፡፡ ለዚህ ቡድን አባልነት የተለየ መለኪያ / መስፈርት/ የለም፡፡ መጫወት የሚፈልግ ሁሉ ይሳተፋል፡፡ በሃብታም እና በድሃ ልጅ፣ በቤት እመቤት እና በቤት ሰራተኛ መካከል ያሉ ልዩነቶች በዚህ ጨዋታ ወቅት ቦታ አይሰጣቸውም፡፡ 

   በዚህ በዓል ቆነጃጅት ሁሉ ከማንኛውም ጊዜ ይበልጥ አዲስ እና የፀዳ ልብስ ለብሰውና ተኳኩለው  የሚታዩበት ዕለት በመሆኑ ለዚህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያሰባስባሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የባህል ልብስ ነው፡፡ ቀሚስ እና መቀነት ያላት የራሷን የሌላት ደግሞ ከዘመድ አዝማድ ተውሳ ታፀዳለች/ታዘጋጃለች/፡፡የጌጣጌጥ አይነቶችንም አስቀድመው ያሰባስባሉ፡፡ እንደ ድሪ ፣ ድኮት ፣ አልቦ ፣ መስቀል እና ሌሎችንም በመዋቢያነት ይጠቀማሉ፡፡

   የሻደይ/አሸንዳ  ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ያስፈልገዋል፡፡ በመጀመሪያ ከሳምንት በፊት የቡድን አመሰራረት ምክክር ይደረጋል፡፡ ቡድኑ በተለያዩ የእድሜ ክልሎች የሚገኙ ልጃገረዶች እና እናቶችን የሚያካትት ነው፡፡ ለዚህ ቡድን አባልነት የተለየ መለኪያ / መስፈርት/ የለም፡፡ መጫወት የሚፈልግ ሁሉ ይሳተፋል፡፡ በሃብታም እና በድሃ ልጅ፣ በቤት እመቤት እና በቤት ሰራተኛ መካከል ያሉ ልዩነቶች በዚህ ጨዋታ ወቅት ቦታ አይሰጣቸውም፡፡ 

   በዚህ በዓል ቆነጃጅት ሁሉ ከማንኛውም ጊዜ ይበልጥ አዲስ እና የፀዳ ልብስ ለብሰውና ተኳኩለው  የሚታዩበት ዕለት በመሆኑ ለዚህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያሰባስባሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የባህል ልብስ ነው፡፡ ቀሚስ እና መቀነት ያላት የራሷን የሌላት ደግሞ ከዘመድ አዝማድ ተውሳ ታፀዳለች/ታዘጋጃለች/፡፡ የጌጣጌጥ አይነቶችንም አስቀድመው ያሰባስባሉ፡፡ እንደ ድሪ ፣ ድኮት ፣ አልቦ ፣ መስቀል እና ሌሎችንም በመዋቢያነት ይጠቀማሉ፡፡
  
    ፀጉራቸውን ማሳመር እና ማስዋብም ሌላው ክዋኔያቸው ነው፡፡ ሹርባ ሰሪዎች ገበያቸው ከሚደራባቸው ቀናት መካከል አንዱ የሻደይ በዓል እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ እያንዳንዱ የዚህ በዓል ተሳታፊዎችም ከቻሉ ግልብጭ ካልሆነ ደግሞ አልባሶ /ጎበዝና ቆነጆ/ የሚባሉትን የሹርባ አይነቶች ይሰራሉ፡፡ ይህ ከተማ እና ከተማ ቀመስ አካባቢዎች ሲሆን በገጠር ያለው ደግሞ ከዚህ የተለየ ነው ፡፡ አብዛኞቹ የሚሰሩት ጋሜ እና ቁንጮ ፣ ሰለላ እና ቅርድድ ሲሆን ይህም ዕድሜን ፣ ያገባ እና ያላገባን በመስፈርትነት በመጠቀም ነው፡፡
 
   የሻደይ ቅጠል ከተማ ያሉት ወደ ገበያ በመሄድ ገዝተው፤ በገጠር ደግሞ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ አካባቢ በማምጣት ይዘጋጃል፡፡ ከዚያም ጨዋታው በመጀመሪያ ቤተክርሰቲያን በመሄድ ታቦቱን የሚያሞግሱ ፣ የቡድን አባላቱን እና ቤተሰቦቻቸውን ለሚቀጥለው ዓመት በሰላም እና በጤና እንዲያደርሳቸው የሚማፀኑበትን ዘፈን ያወርዳሉ፡፡ ከዚያም በየቤቱ በመዘዋወር ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ………

በወቅቱ ከሚገጠሙ ስንኞች መካከል ፡-

   አሽከር ይሙት ይሙት ይላሉ የኔታ
    አሽከር አይደለም ወይ የሚያደርገው ጌታ

  ከጌታዬ ደጃፍ ወድቄ ብነሳ
   የሰራ አካላቴ ወርቅ ይዞ ተነሳ

F   እሷ ቀጭን ፈታይ ባሏ መልበስ ያውቃል
   እሰይ የኔ ጌታ በሩቅ ያስታውቃል፡፡ እነዚህ እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
    
   ይህ ጨዋታ በአካባቢው ልጃገረዶች እና በጎብኚዎች ተናፋቂ እና ቶሎ ባያልፍ የሚሰኝ በመሆኑ እርስዎም ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በመሄድ የዚህ በዓል ታዳሚ በመሆን ራስዎን ያዝናኑ፡፡

No comments:

Post a Comment