ደጉ ደበበ ከእነሊዮኔል ሜሲ፣ ኔይማር ፣ ማራዶና እና ዚነዲን ዚዳን ጋር እንዲጫወት ከሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖፕ ፍራንሲስ እና ከተጨዋቹ ሃቪየር ዛኔቲ ፊርማ ያረፈበት የጥሪ ደብዳቤ ደርሶታል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞው አምበል ደጉ ደበበ ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ጣልያን እንደሚጓዝ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ አስታወቀ። ደጉ ደበበ የአለም ታላላቅ ተጨዋቾች በሚሳተፉበት እና ለአለም ሰላም በተዘጋጀው የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ በቅርቡ ወደ ጣልያኗ ሮም ከተማ እንደሚያመራ ታውቋል፡፡
ጨዋታው 'Inter-religious Match for Peace' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ በጨዋታው ላይ ደጉ ደበበን ጨምሮ ሊዮኔል ሜሲ፣ ኔይማር ፣ ማራዶና ፣ ዮሲቤናዩን ፣ ዚነዲን ዚዳን እና ሌሎችም ተጨዋቾች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህንን አሰመልክቶም ደጉ «በዚህ ጨዋታ ላይ እንድሳተፍ በፖፕ ፍራንሲስ እና በዛኔቲ ስለተጋበዝኩ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል” ብሏል ፡፡
በጨዋታው የሚተላለፈው መልዕክትም ትልቅ ነገር ነው ፤ ሁሉም የአለም ሃይማኖቶች ለአለም ሰላም እንዲሰሩ የሚያደርግ በመሆኑና በዚህ ላይም ተሳትፎ በማድረጌ ደስ ብሎኛል» ሲል ገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. መስከረም 1 ቀን በጣለሊያኗ ሮም ከተማ ኦሎምፒክ ስታዲየም ጨዋታው ይካሄዳል፡፡
No comments:
Post a Comment