Tuesday, May 27, 2014

የማይጨው ጦርነት / 1928 – 1933/

 
  
 ፋሽስት ጣሊያን በ5 ዓመታት ወረራ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰችው ጥፋት ከፍተኛ ነው፡፡ ላደረሰችው ለዚህ ጥፋትም በጠቅላላው 185 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ወይም 326 ቢሊዮን ሊሬ ካሳ እንድትከፍል ተጠይቃ በመጨረሻ በተደረገው የፓሪሱ ስምምነት መሰረት 6 ሚሊዮን 250 ሺ ፓውንድ ስተርሊንግ  ወይም 10 ቢሊዮን ሊሬ እንድትከፍል ተደርጓል፡፡ ይህ ገንዘብ በዚያን ጊዜ በነበረው የምንዛሬ መጠን ወይም በነሲብ እንደተነገረው ከሆነ  16 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ ዶላር ነበር ፡፡

  ይህ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር 30 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቁሟል ፡፡ እዚህ ላይ በወቅቱ ያለውን የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም /የምንዛሬ ጥንካሬ / ማየት ተገቢ ይሆናል ፡፡ በዚያን ጊዜ በሚስጥር ተይዞ የነበረ ቢሆንም የቆቃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ የተሰራው ጣሊያኖች በከፈሉት 30 ሚሊዮን ብር ነው ፡፡ ይህም ገንዘብ የደም ካሳ ተብሎ የተከፈለ እንደነበር ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡
      
    ምንጭ ፡- / ኢትዮጵያ ሀገሬና ትዝታዬ /
  
  43.2 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው  የቆቃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በ1952 ዓ.ም ከአ.አ በስተደቡብ ምስራቅ በ80 ኪ.ሜ ርቀት በአዋሽ ወንዝ ላይ ተገነባ፡፡


  የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ አማካሪ መሀንዲስ ኖር ኮንሰልታንት /Norconsultants, oslo , Norway / የሚባል የኖርዌይ ኩባንያ ሲሆን ፕሮጀክቱ በ1949 ዓ.ም ተጀምሮ በ1952 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ የቆቃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ከ1952 - 2002 ዓ.ም 50ኛ አመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በአሉን ከዛሬ 4 አመት በፊት አክብሯል ፡፡ 

የቆቃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ

No comments:

Post a Comment