Monday, August 18, 2014

ነሀሴ 12 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የተወለዱባት ዕለት ናት


   ምኒልክ ከአባታቸው ንጉስ ኃይለመለኮት እና ከእናታቸው / እጅጋየሁ ነሐሴ 12/ 1836 . ዕለተ - ቅዳሜ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ቀበሌ ልዩ ስሟ እንቁላል ኮሶ በምትባል ቦታ ነው የተወለዱት፡፡ ክርስትና የተነሱት ደግሞ አያታቸው ንጉስ ሳህለስላሴ ባሰሯት ጥንታዊቷ የአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ሲሆን የሸዋ ንጉስ ሆነው ከቆዩ በኃላ 1881 . የኢትዮጵያ ንጉሰ - ነገስት በመሆን ዘውድ ደፍተዋል፡፡ ታኅሳስ 3 ቀን 1906 .. ዕለተ ዓርብ ደግሞ በህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
  ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ 1888. የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ በማስተባበር ወራሪውን የጣልያን ጦር አድዋ ላይ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን በቅኝግዛት ያልተያዘች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ያደርጋታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ መዲና ለመሆን የበቃችውን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባን በዘመናዊ መዋቅር የቆረቆሩት አፄ ምኒልክ፤ በኢትዮጵያ በርካታ አዳዲስ ጅማሮዎችን በመፍጠር ጉልህ ሚና አላቸው፡፡


  በግብፆች አስተዳዳሪነትአቢሲኒያ ባንክበሚል ስያሜ የመጀመሪያውን ባንክ፤ የመጀመሪያውን ፖስታ ቤትአራዳ ፖስታ በኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ትብብር የተሰራው የመጀመርያው የባቡር መንገድ፣ የመጀመርያዎቹ የስልክና የቴሌግራፍ አገልግሎቶች፤ የመጀመርያው የሞተር መኪና፤ የመጀመርያው የውሃ ቧንቧ እንዲሁም በመንግሥት አስተዳደር የመጀመርያው የሚኒስትሮችን ካቢኔ አቋቁመዋል፡፡

በትውልድ ቦታቸው በደርግ ዘመነ መንግስት የተሰራላቸው ሀውልት 


No comments:

Post a Comment