የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፥
ለመደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥቡ ለወንዶች 2 ነጠብ 57 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፥ ለሴቶች ሴት የማታ ተማሪዎችን
ጨምሮ 2 ነጥብ 14 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።
በሁሉም አርብቶ አደር አከባቢዎችና ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ደግሞ ለወንዶች 2 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፥ ለሴቶች 2 ነጠብ 14 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።ለአይነ ስውራን /መስማት ለተሳናቸው/ ለሁለቱም ፆታዎች የመግቢያ ነጥቡ 2 ነጥብ 14 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።

በሁሉም ክልሎች የግል ተፈታኞች ለወንዶች የማታ ተማሪዎችን ጨምሮ 2 ነጥብ 86 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች ደግሞ 2 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ተደርጓል። በ2006 የትምህርት ዘመን 888 ሺህ 417 ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል የመልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፥
ከእነዚህ መካከል ወደ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ያለፉት 271 ሺህ 839 መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ካለፉት ተማሪዎች መካከልም 50 ነጥብ 6 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ብሏል ። በመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ከሚገቡት ተማሪዎች መካከል 70 በመቶዎቹ በተፈጥሮ ሳይንስና ፣ 30 በመቶዎቹ ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ የሚመደቡ ይሆናል።

No comments:
Post a Comment