ከሰሞኑ ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የዜና አዉታሮች ባዉጡት መረጃ መሰረት እዉቁ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ሊቅ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በቤሩት ከተማ በተካሄደው አለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያን በጃዝ ሙዚቃ አስተዋውቋል ፣ የኢትዮጵያን ባህልም አሳይቷል ፡፡ በተለይ አርቲስቱ የሚታወቅበትን የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት በሽዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ፣ ታዋቂ ሙዚቀኞች ፣ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች በተገኙበት ነበር ያቀረበው፡፡ በዝግጅቱም ልክ እንደ አትሌቶቻችን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲዉለበለብ አድረጓል ፡፡ ሙዚቃችንም በአለም አቀፍ መድርክ ከፍ እንዲል አስችሏል ፡፡
በተመሳሳይም አርቲስቱ በካናዳ ሞንትሪል አለም አቀፍ የጃዝ ፌስቲቫል ኢትዮጵያን በመወከል ስሞኑን መሳተፉ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ሙሉ የሙዚቃ ባንዱን በመያዝ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት የመድረክ ዝግጅቱን አቅረቧል፡፡ በዚህ አለም አቀፍ የጃዝ ፌስቲቫልም እዉቅ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፈዉበታል፡፡ ለምሳሌ እዉቁ ፒያኒስት ኬስ ጃኔት ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ቶን ቤኔት ፣ ሪታ ፍራንክሊን ፣ ዲያና ሮዝ ፣ ታዋቂዉ የብሉዝ ድምፃዊ ቤቤ ኪንግ እና ሌሎች የሙዚቃ ሰዎችም አብረዉት ነበሩ ፡፡
No comments:
Post a Comment