Tuesday, August 26, 2014

የብሄራዊ ቲያትሯ መሪ ተዋናይ አርቲስት አስካለ አመነሸዋ 90ኛ አመት ተከበረ፡፡



   የአርቲስቷ 90ኛ አመት ልጃቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሌሎችም በተገኙበት አቧሪ በሚገኘው ቤታቸው በድምቀት ተከብሯል፡፡ የ5 ልጆች እናት የሆኑት አርቲስት አስካለ  ሽቅርቅር እና ጨዋታ አዋቂ ናቸው፡፡ 

  ልጃቸው አቶ ታቦርም ስለ እናቱ ሲናገር “ደስታ፣ ሳቅ እና ጨዋታ የእሷ መለያ ናቸው” ብሏል፡፡ እኛም በቦታው ተገኝተን ይህንንው ነው የታዘብነው፡፡ 

  የብሄራዊ ቲያትሯ መሪ ተዋናይ አርቲስት አስካለ አመነሸዋ ከትወናው አለም እስከተገለሉበት ጊዜ ድረስ “ሂሩት አባቷ ማን ነው…?” ን ጨምሮ 40 በላይ ቲያትሮች ላይ ተውነዋል፡፡ ስነ-ስቅለት፣ ቴዎድሮስ፣ ስስታሙ መንጠቆ፣ አስቴር፣ ጎንደሬው /ማሪያም፣ አወናባጅ ደብተራ፣ ምኞቴ፣ የሺ፣ እኝ ብዬ መጣሁ፣ ለሰው ሞት አነሰው፣ ኦቴሎ፣ የበጋ ሌሊት ራዕይ፣ የከተማው ባላገር፣ ጠያቂ እና የአዛውንቶች ክበብን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ 

  በአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ነጋሽ /ማሪያም የተደረሰው የአዛውንቶች ክበብ የመጨረሻ ስራቸው እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ 


   ቀደም ባለው ጊዜ ከንጉሰ ነገስቱ የአንገት ሀብል፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ “የሂሩት አባቷ ማን ነው” 50ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ ዋንጫ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡


  የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ ….. አይደል ያለው ቴዲ አፍሮ በዘፈኑ፡፡ እኛም ቀደምቶቻችንን እናስብ፤ እነሱንም እንጠይቅ፣ እንመርምር ብዙ ቁምነገሮችንም እናገኛለንና…….

No comments:

Post a Comment