Thursday, August 7, 2014

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለሦስት የግል አየር መንገዶች ፈቃድ ሰጠ ፡፡


     የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮለኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ባለፈው ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለስልጣኑ በ2006 በጀት አመት ለ3 የግል አየር መንገዶች  “ኤር ኦፕሬተር ሰርተፊኬት” መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

      አየር መንገዶቹ መደበኛ ያልሆነ የመንገደኛ እና የጭነት በረራ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ፍቃድ ያገኙት እነዚህ አየር መንገዶች ኖጎቭ አቪዬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሆርን ኤክስፕረስ ኤርላይንስ እና ሉሲ ኤርላይንስ በመባል ይታወቃሉ፡፡

     በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገቡ የግል አየር መንገዶች ቁጥር 15 ደርሷል፡፡ከእነዚህ ውስጥ በትክክል አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት 8 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡
   የተመዘገቡት አየር መንገዶች ቁጥር 26 ደርሶ እንደነበር ያስታወሱት ኮለኔል ወሰንለህ፣ አብዛኞቹ ፍቃዱን ይዘው ለረዥም ዓመታት ስራ ሳይሰሩ በመቀመጣቸው ባለስልጣኑ የተወሰኑ ፍቃዶችን መሰረዙን አስታውቀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment