Friday, August 22, 2014

ኢትዮጵያን አትሌቶች ድል እየቀናቸው ነው፡፡


   ቶክ ሆልም ላይ በተደረገ የ5 ሺህ ሜትር ዲያመንድ ሊግ ውድድር ሙክታር እንድሪስ የመቱን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ በ1ኛነት አጠናቋል። ሙክታር ውድድሩን ነሐሴ 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተካሄደው 12ኛው ዙር ለመጨረስ 12፡54.83 ሰዓት ፈጅJቶባታል፡፡ ይህም ሰዓት በዚህ ርቀት የአመቱ ፈጣን ሰዓት በመሆን ተመዝግቦለታል። 
 በጎርጎሮሳውያኑ 2012 የ5 ሺህ ሜትር የአለም ወጣቶች ሻምፒዮና የነበረው ሙክታር በስቶክ ሆልም ያሳየው ብቃት አስደናቂ ሆኗል። ከውድድሩ በኋላ ሙክታር “ይህ ውጤት ለእኔ ምርጡ ሰዓቴ ከመሆኑም ባለፈ የዚህ አመት ፈጣኑ ሰዓት ሆኗል፤ ስለዚህ ምሽቱ ለእኔ መልካም ነበር” በማለት አስተያቱን ሰጥቷል።
  በዲያመንድ ሊጉ በ5 ሺህ ሜትር የኔው አላምረው በ14 ነጥብ እና ሙክታር እንድሪስ በ8 ነጥብ እየመሩ ሲሆን፣ሀጎስ ገብረሕይወት 5 ነጥብ ይዞ ምድቡ ውስጥ ይገኛል።
   በተያያዘ ዜና በሴቶች 1 ሺህ 5 መቶ ሜትር ውድድር ሲካሄድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናዋ ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡ ገንዘቤ በውድድሩ ላይ ቆይታ ነው በኔዘርላዳዊቷ ተቀድማ ሁለተኛ ለመሆን የተገደደችው። ውድድሩን ለማጠናቀቅ ገንዘቤ 4፡01.00 ሰዓት ሲፈጅባት በአንደኝነት ያጠናቀቀችው ሲምፕሰን 4፡00.38 በሆነ ሰዓት ውድድሯን አጠናቃለች። ገንዘቤ ዲባባ በ1 ሺህ 5 መቶ ሜትር ብትሸነፍም በ10 ሺህ ሜትር በተመሳሳይ 10 ነጥብ ከኬንያዊቷ ችሮኖ ሜርሲ ጋር እየመሩ ነው።ብዙም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በማይገኙበት የመሰናክል ሩጫ ትላንት በተካሄደው ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ አሸናፊ ሆናለች።
    በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ውድድር የተካፈለችው ሕይወት አያሌው በአንደኝነት ስታሸንፍ 9፡17.04 በሆነ ሰዓት ነው።

No comments:

Post a Comment