የ2007
የትምህርት ዘመን በመንግሥትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ በሚከተለው መልኩ ተወስኗል፣
1ኛ. በግል ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማት በቀን፣ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማታና እንዲሁም በርቀት ትምህርት ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉት 250 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ይሆኖሉ፡፡
2ኛ. በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት በመደበኛ የትምህርት ዘርፍ ገብቶ ለመማር ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት ቅደም ተከተል በውድድር ይሆናል፡፡
በመሆኑም
፡-
ሀ/ በተፈጥሮ
ሳይንስ ዘርፍ
· ሁሉም መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች 315 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ፣
·
በአዎንታዊ ድጋፍ
·
ሁሉም ሴት ተማሪዎች /የታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ /
300 እና ከዚያ በላይ ያመጡ፣
·
ሁሉም የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር አካባቢ ወንድ ተማሪዎች 305 እና
ከዚያ በላይ ያመጡ፣
·
ሁሉም መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች 300 እና ከዚያ በላይ ያመጡ፣
· ሁሉም
የግል ተፈታኝ ወንድ ተማሪዎች 320 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ፣
· ሁሉም
የግል ተፈታኝ ሴት ተማሪዎች 315 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ
ይሆናሉ፣
ለ/ በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ
፡-
·
ሁሉም መደበኛና የማታ ተማሪዎች 280 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ
·
በአዎንታዊ ድጋፍ፡-
-
ሁሉም ሴት
ተማሪዎች /የታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ/
270 እና ከዚያ በላይ ያመጡ፣
-
ሁሉም የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር አካባቢ ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ፣
-
ሁሉም መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ፣
-
ሁሉም አይነ ስውራን ተማሪዎች 230 እና ከዚያ በላይ፣
·
ሁሉም የግል ተፈታኝ ወንድ ተማሪዎች 285 እና በላይ ያስመዘገቡ፣
·
ሁሉም የግል ተፈታኝ ሴት ተማሪዎች 282 እና በላይ ያስመዘገቡ ይሆናሉ፡፡
ምንጭ፡- www.nae.gov.et
No comments:
Post a Comment