Sunday, April 28, 2013

የዳግማዊ ሚኒልክ ሞት!


ዳግማዊ አጼ ሚኒልክ ሕመሙ ፀንቶባቸው ነበርና ታህሳስ 3 ቀን 1906 ዓ.ም በዕለተ ዓርብ ሞቱ፡፡ ወዲያው እንደሞቱ የግቢ ሥራ ቤቶች ለቅሶ ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን የልጅ ኢያሱ ባለሟሎች አገር እንዳይሸበር ሰግተው በቶሎ ዝም አሰኙዋቸው፡፡ አቤቶ ኢያሱ በዚያ ዕለት ፍልውሃ በመታጠቢያ ቤታቸው ውስጥ ነበሩ፡፡ የአባታቸውን የአጼ ሚኒልክ ሞት በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ወደቤታቸው ወጡና ተቀመጡ፡፡ ሆኖም አገርእንዳይሸበር በማለት ሐዘናቸውን በይፋ አላሳዩም፡፡

       እንዲያውም አንዳች ሐዘን አለመኖሩን ለማስረዳትና ለማሳመን ሲሉ በማግስቱ ቅዳሜ ወደ ጃንሆይ ሜዳ ወጥተው ከአሽከሮቻቸው ጋር በፈረስ ጉግስ ሲጫወቱ ዋሉ፡፡ ይህም ለአገር ፀጥታ ሲባል ምሥጢር ሆኖ ተደበቀ፡፡ የአፄ ሚኒልክ አስክሬን አሽከሮቻቸው አምሮ በተሰራ በብረት ሳጥን አድርገው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ባለችው በሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አጠገብ በልዩ ሆኖ በተሠራውቤት ውስጥ በክብር አስቀመጡት፡፡

     ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱና ልጃቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ከዚያ ይለዩ ዳዊት እየደገሙ ያለቅሱ ነበር፡፡አፄ ሚኒልክ በ1881 መጋቢት ወር የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን የያዙ ሲሆን በድምሩ24 ዓመት ከዘጠኝ ወራት በንጉሡ ነገሥትነት ሥልጣን ቆይተዋል፡፡ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱና ልጃቸው ወ/ሮ ዘውዲቱ ስለምኒልክ ሞት ስንኝ ቋጥረዋል፡፡

የወ/ሮ ዘውዲቱ ግጥም
ቀድሞ የምናውቀው የለመድነው ቀርቶ
እንግዳ ሞት አየሁ ከአባቴ ቤት ገብቶ፡፡
እጅግ ያስገርማል ያስደንቃል ከቶ
ከሁለታችን በቀር እሚያውቀው ሰው ጠፍቶ፡፡
ምልክቱ ይህ ነው የንጉሥ ሞት ሐዘን
ጣይቱ ስትጨልም ጨረቃ ደም ስትሆን
ወልደውኛል እንጂ እኔ አልወለድሁዎ
አንጀቴን ተብትበው ምነው መያዝዎ፡፡
እጅግ አዝኛለሁ አላቅሰኝ አገሬ
የሁሉ አባት ሞቶ ተጎድተሃል ዛሬ፡፡
ድርቅ ሆኗል አሉ ዘንድሮ አገራችሁ
ዝናሙ ሲጠፋ ምነው ዝም አላችሁ፡፡
አሻግሬ ሳየው እንዲያው በሰው ላይ
መከራም እንደሰው ይለመዳል ወይ፡፡
ያች የሰጡኝ በቅሎ መጣባት ባለቤት
አልገዙም መሰለኝ ሊገለኝ ነው እፍረት፡፡

የእቴጌ ጣይቱ ግጥም
እምቢልታ ማስነፋት ነጋሪት ማስመታት ነበረ
ሥራችን
ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ተራችን፡፡

                       የ20ኛው ክ/ዘመን መባቻ ከመርስዔ ሐዘን ወልደቂርቆስ

Friday, April 26, 2013


Le Figaro Names Three Ethiopians to ‘Africa’s 15 Most Powerful Women’ List



New York (TADIAS) – Le Figaro has named three Ethiopians to its list of Africa’s 15 most powerful women, including the long distance track athlete and three-time Olympic champion Tirunesh Dibaba, and Bethlehem Tilahun Alemu, the founder and CEO of the international Ethiopian shoe brand SoleRebels.
The French newspaper also selected Ethiopian-born model Liya Kebede who lives in the United States among Africa’s power women. Other leaders include Ellen Johnson Sirleaf, the current President of Liberia, as well as the South African actress and fashion model Charlize Theron, and Kenyan activist, lawyer, and blogger Ory Okolloh who works as Google’s Policy Manager for Africa.

Thursday, April 25, 2013

ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ

የደራሲው ሥራዎች
1.  ፍቅር እስከመቃብር(ልቦለድ)
2.  ትዝታ(ታሪክ)
3.  ወንጀለኛው ዳኛ(ልቦለድ)
4.  የሕልም እዣት(ልቦለድ)
5.  ተረት ተረት የመሰረት(ወግ)
6.  የትምህርትና የተማሪ ቤት ትርጉም(ትምህርት)
7.  ያበሻና የወደኋላ ጋብቻ(ተውኔት)
       
(1902 - 1996)
ሀዲስ ዓለማየሁ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ አውራጃ ከየኔታ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን  ለቤተሰባቸው ብቸኛ ልጅ ናቸው። ሀዲስ እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በቤተሰባቸው አጠገብ እና በአባታቸው ሀገር ደብረ ኤልያስ ሄደው ከባህላዊ የግዕዝ ት/ቤት ዜማ ተምረዋል፥ቅኔ ተቀኝተዋል። በ1918 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ የመጡት ሀዲስ፥በዚያው አመት በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርታቸውን ተከታትለው በኢጣሊያ ወረራ ዋዜማ በአዲስ አበባ በመምህርነት በጎጃም በጉምሩክ ሥራ ባለሙያነት ሠርተዋለል።

   በኢጣሊያ ወረራ ወቅት 1929-1933 ዓ.ም. ከልዑል ራስ አምኃ ኃ/ስላሴ ጦር ጋር በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በምእራብ ኢትዮዽያ በጣሊያን ተማርከው፥ ወደ ኢጣሊያ በግዞት ከቆዩ በኋላ በ1936 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው በነፃነት ተመልሰዋል። ከነፃነት በኋላ ዘመናዊት ኢትዮዽያን ለማደራጀት በተደረገው ትግል በማስታወቂያ ሚኒስቴር 1936፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - በኢየሩሳሌም 1937-1939 እና በተ.መ.ድ 1939-1946፥ በእንግሊዝ 1948፥ እንደገና በተ.መ.ድ 1949-1953 ሀገራቸውን በአምባሳደርነት ያገለገሉ ሲሆን በዚሁ "ወርቃማ" የሥራ ዘመናቸው በመዲናችን አዲስ አበባ- የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ECA እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ክቡር ኢትዮዽያዊ ናቸው።  ከ1953 ዓ.ም. የታኅሣሡ መፈንቅለ መነግስት ሙከራ በኋላ እስከ 1961 ዓ.ም. ድረስ በሚኒስትርነት ማእረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የመማክርት ጉባኤ አባል  ከ1961 - እስከ 1966 ድረስ በሀገሪቱ ፓርላማ የህግ መወሰኛ ም/ቤት አባል ከ1966 ጎጃም ሕዝብ በመረጣቸው መሰረት የብሄራዊ ሸንጎ አባል 1966-1968 ሆነው ያገለገሉት ሀዲስ ዓለማየሁ "ኢትዮዽያ ምን አይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል?" በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ሀገራቸው ያላቸውን የመልካም አስተዳደር ራእይ ተመልክቶ ደርግ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንዲሰሩ ጠይቋቸው አለመቀበላቸው ተነግሯል።

ሀዲስ አለማየሁ በ1929 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ካዘጋጁዋት "ያበሻና የወደኋላ ጋብቻ" በኩር የተውኔት ድርሰታቸው ፋቡላ አንስቶ "ተረትተረት የመሰረት" 1948 "ፍቅር እስከመቃብር" 1958  ወንጀለኛው ዳኛ 1974  "የልምዣት" 1984 በተሰኙት የረዥም ልቦለድ ሥራዎቻቸው በተጨማሪ ያልታተሙ ድርሰቶችም አሏቸው። የኢትዮዽያን ዘመናዊ ሥነጽሑፍ በአያሌው የታደጉ "የቀለም ሰው" ናቸው።

ሀዲስ ዓለማየሁ "ፍቅር እስከመቃብር" በተሰኘው የአማርኛ ረዥም ልቦለድ ሥራቸው "ለኢትዮዽያ ሥነጽሁፍ አዲስ ምእራፍ ከፋች!" የሚል ሞገስ ያገኙ ሲሆን፥ በዚሁ ኪናዊ ሥራቸውም ፋሽስት ኢጣሊያ ከወጣ በኋላ ብዚዎቹ ኢትዮዽያውያን ደራስያን ያላተኮሩበትን የፊውዳል ኢትዮዽያን ገፅታ በተለየ ትኩረት በስፋትና በጥልቀት በመዳሰስ ኪናዊ በሆነ የቋንቋ ኃይልና ውበት የገለጹ፥ በፊውዳሉ ሥርዓት ላይ ያመፁ እንደ ጉዱ ካሣ ፥ በዛብህ ፥ ሰብለወንጌል አበጀን የመሳሰሉ ሕይዋን ገፀባሕርያት በመሳል - በለውጥ የትግል መንፈስ ላይ ለነበረው አዲስ ትውልድ ሀዲስ ራዕያቸውን በጥበብ አጋርተዋል።

      በአጻጻፍ ብልሃቱ በአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ አዲስ ፈር የቀደደው የ"ፍቅር እስከ መቃብር" ድርሰታቸው በሁለት የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሟል "አዲስ ዓለም አሳየን!" የሚል ሞገስ ያገኙት ሀዲስ ዓለማየሁ በ1960 ዓ.ም የቀ.ኃ.ሥ. ሽልማት ክብር በሥነጽሁፍ ዘርፍ በ1962 ዓ.ም. ተሸልመዋል፡፡ ነሐሴ 27 ቀን 1991 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክትሬት ዲግሪም አግኝተዋል። "ትዝታ" 1985 በሚለው ግለ ታሪካቸው ሰብዕናቸውን የተረኩልን ታረክ ፀሐፊ፥ አርበኛ መምህር፥ አምባሳደር፥ ሚኒስትርና የሥነ ጽሑፍ ጠቢብ  ሃዲስ ዓለማየሁ "የኢትዮዽያ ሥነ ጽሑፍ አባት!" የሚል የሀያስያንና የሕዝብ ሞገስ አግኝተው ኅዳር 28 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው አረፉ።

                                    ምንጭ:ብርሀነ መስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር። 

ሲሳይ ንጉሱ




የደራሲው ሥራዎች

  • ጉዞው (1975 )
  • ሰመመን (1978 )
  • ግርዶሽ (1981 )
  • ትንሣኤ (1983 )
  • የቅናት ዘር (1988 )
  • ረቂቅ አሻራ (1995 ዓ.ም.)

 ስለደራሲው በጥቂቱ

 አዲስ አበባ በ፲፱፶፩ .. የተወለዱት ሲሳይ ንጉሡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባልቻ አባነፍሶ፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ተከታትለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ከ፲፱፸፬-፲፱፸፯ .. ድረስ ተምረዋል።

   
በዩኒቨርሲቲ ሕይወት ዙሪያና በፍቅር ታሪክ ላይ በሚያተኩረው ሰመመን በሚባለው መጽፈሐፍቸው በብዙዎች ዘንድ የታወቁት ሲሳይ ንጉሡ፣ ጉዞው፣ ግርዶሽ፣ የቅናት ዛር የተባሉ ረጃጅም ልብወለዶች አሏቸው፡፡ ጉዞው የሚለውን ኖቬላ ጨምሮ ሌሎች አጫጭር ልብወለዶችን ጽፈዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሥነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ሽልማት በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ1991.ም. ተሸላሚም ሆነዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የደራሲያን ማኀበር ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
 

 



  በወላይታ ሶዶ 4.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

   

    ሚያዚያ ፣ 16 ፣ 2005  በትናንትናው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማና አካባቢዋ ላይ የተከሰተው ቀላል የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ምንም አደጋ እንዳላደረሰ የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝም መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

    የቢሮው አስተባባሪ አቶ አብርሃም ኦቾሬ እንዳሉት የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.0 የተመዘገበ ነው።

  
     የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አታላይ አየለ  መሰል የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ባሉ ከተሞች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው ብለዋል። ይህ በመሆኑም በአካባቢዎቹ የሚገነቡ ሀንጻዎች ላይ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

Sunday, April 21, 2013


ጸጋዬ ከበደ የለንደን ማራቶንን አሸነፈ



ሚያዚያ 13 ፣ 2005  በተካሄደው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው ጸጋዬ ከበደ አሸነፈ።
ጸጋዬ በ2 ሰአት ከ6 ደቂቃ ከ03 ማይክሮ ሰከንድ ነው ውድድሩን በአንደኛነት ያጠናቀቀው።
ሌላው ኢትዮጵያዊ አየለ አብሽሮ ሶስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ  ፈይሳ ሌሊሳ  ውድድሩን አራተኛ ሆኖ አጠናቋል።
 
   ውድድሩን በአብዛኛው ሲመራ የቆየው ኬንያዊው ኢማኑኤል ሙታይ በሁለተኝነት ጨርሷል።


የሴቶቹን ውድድር ኬኒያዊቷ ፕሪስካ ጄፕቱ በአንደኛነት አጠናቃለች።  ይህ በእንዲህ እንዳለ የለንደን ኦሎምፒክ ባለወርቅ ሜዳሊያ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና  ፥ ጆሽ ኬስዲ ከተባለ ካናዳዊ የዊልቸር ተወዳዳሪ ጋር በመጋጨቷ ውድድሩን 16ኛ ሆና ነው ማጠናቀቅ የቻለችው  ።
እንኳን ደስ አለህ … ስለ አኮራህን የሀገራችንንም ስም ስላስጠራህ ከልብ እናመሰግናለን !
Tsegaye Kebede wins men's London Marathon
 
The legendary days of great Ethiopian Marathon runners seems to be revived all over again. In less than a month three Ethiopian athletes have won three major Marathons, Tilahun Regassa Rotterdam his fellow Ethiopian Getu Feleke was second for the second straight year, Lelisa Desisa Boston and now Tsegaye Kebede London.

Tsegaye Kebede won the second men's London Marathon of his running career in the English capital this afternoon.
The Ethiopian, who won the event back in 2010, looked as though he had left himself with too much ground to make up with five miles left to run.
     However, he was able to hit the front in the closing stages and he eventually won through in two hours, six minutes and four seconds. As well as his victory three years ago, the 26-year-old finished third in 2012 and second in 2009.

    Tsegeye Kebede's life story is the sort that Hollywood producers bin as too far-fetched. The fifth of 13 children, he was brought up in poverty in Gerar Ber, 40km north of Addis Ababa, collecting firewood and herding livestock to earn about 20 pence a day. He ate one meal a day.

Friday, April 19, 2013


የመጀመሪያው የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል በአዲስ አበባ ተከፈተ

 
  በአፍሪካ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ለመከላከል እገዛ የሚያደርግ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የአፍሪካ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን በዳዳ እና የአየር ንብረት ሳይንስ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ዘውዱ እሸቱ በሰጡት መግለጫ ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ ኢትዮጵያ በአደጋና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያደረገች ያለውን ተግባር ያጠናክራል ብለዋል፡፡
 
      ማዕከሉም በዋናነት በአደጋ ስጋት አመራር ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ክፍተትን ለመሙላትና በአየር ንብረት ለውጥና በአደጋ ስጋት መከላከል ላይ በትብብር ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም የመረጃ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በማዕከሉ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን ለአደጋ ስጋት ለሆኑ አካባቢዎች የራሱን ሚና እንደሚወጣም ጠቁመዋል፡፡ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል ራሱ በሚያከናውናቸው የምርምርና የስልጠና ተግባራት ገቢ ያመነጫል፡፡