ሁለት ዓለማቀፍ የፊልም ሽልማቶችን ያሸነፈው የዘረሰናይ መሃሪ ፊልም “ድፍረት” የፊታችን ረቡዕ ነሐሴ 28 ቀን
2006 ዓ.ም በብሄራዊ ትያትር እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡
2014ቱ የሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ወርልድ ሲኒማ ድራማቲክ ኦድየንስ አዋርድን እና የበርሊን ዓለማቀፍ የፊልም ፌስቲቫሉን ፓኖራም ኦዲየንስ አዋርድን ያሸነፈው “ድፍረት” ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ፊቸር ፊልም ነው፡፡
2014ቱ የሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ወርልድ ሲኒማ ድራማቲክ ኦድየንስ አዋርድን እና የበርሊን ዓለማቀፍ የፊልም ፌስቲቫሉን ፓኖራም ኦዲየንስ አዋርድን ያሸነፈው “ድፍረት” ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ፊቸር ፊልም ነው፡፡
የፊልሙ ፕሮድዩሰር የሆነችው ምሕረት ማንደፍሮ ፊልሙን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስመረቅ መዘጋጀታቸውና በተከታይም ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሲኒማ ቤቶች ሊታይ መሆኑ ስሜት እንደፈጠረባት ተናግራለች፡፡
የፊልሙ ኤክሲክዩቲቭ ፕሮድዩሰር ታዋቂዋ የሆሊዉድ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በበርካታ ዓለማቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ የታየው “ድፍረት” ጠላፊዋን በመግደሏ ሳቢያ ለእስር በተዳረገች ታዳጊ ታሪክ እና ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኋላ ከእስር ባስፈታቻት የሕግ ባለሞያ (መዓዛ አሸናፊ) ታሪክ ላይ የሚያተኩር ፊቸር ፊልም ነው፡፡