Friday, February 7, 2014

የቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የማስፋፊያ ግንባታ ሊጀመር ነው

     
      የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን የማስፋፊያ ግንባታ ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቀቀ። የማስፋፍያ ግንባታው ከቻይናው ኤግዚም ባንክ በተገኘ 250 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚከናወን መሆኑን የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ገልጿል። የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ የማስፋፊያ ዲዛይን ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ግንባታ ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
 
   በየአመቱ የአየር ትራፊክ ፍሰቱ ከተጠበቀው በላይ ዕድገት በማሳየቱ የአውሮፕላን ማረፊያው ከአቅም በላይ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት መገደዱን ነው ሃላፊው ያመለከቱት። በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ ፍሰት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስተናገድም የማስፋፍያ ፕሮጀክቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
 
   የማስፋፊያ ግንባታውን የቻይናው የተባለ ኩባንያ የተረከበ ሲሆን የግንባታው ተቆጣጣሪ መሃንዲስ  ደግሞ የተባለ የሲንጋፖር አማካሪ ድርጅት እንደሆነ ገልጸዋል። ድርጅቱ የማስፋፊያ ግንባታ ከማከናወን ባሻገር ከቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በእጅጉ የላቀና ደረጃውን የጠበቀ አማራጭ ኤርፖርት ለመገንባት በሞጆ ዱከም እና ተፍኪ በተባሉ አካባቢዎች ቅድመ ጥናት ስራዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment