Monday, February 17, 2014

193 መንገደኞችን ጭኖ ወደ ሮም ሲያመራ የነበረ የአትዮጵያ አውሮፕላን ተገዶ ጄኔቫ በሰላም አረፈ

     አውሮፕላኑ ተገዶ ወደ ሮም ሲያደርገው የነበረውን በረራ ቀይሮ ወደ ሲዊስዘርላድ  በማምራት ጄኔቭ እንዲያርፍ በጠላፊዎቹ  በተገደደው መሰረት የበረራ ቁጥር ኢት-702 በጄኔቫ አየር መረፊያ ያለምንም ጉዳት በሰላም አርፏል፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድረገጹ ባወጣው ሰበር ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ምንም አይነት የተጎዳ ተጓዥ እንደሌለ አስታውቋል፡፡ አውሮፕላኑ በውስጡ 193 መንገደኞችም አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን ፣ከዚህ ውስጥ 140 ተጓዦቹ ጣሊያናውያን ነበሩ፡፡ አየር መንገዱ በደረሰበት እገታ ጄኔቫ እንዲያርፉ የተገደዱ ተጓዥ ደንበኞቹን ወደ መዳረሻቸው በሰላም እንዲደርሱ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሆንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

    የጄኔቫ አውሮፕላን ማረፊያ በአሁኑ ወቅት ዝግ ሲሆን ፖሊስ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰና ሁኔታውም በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል፡፡ አንድ ጠላፊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለም ታውቋል፡፡ በሚንስትር መአረግ የመንግስት ኮምኒኬሽን ሀላፊ የሆኑት ሬድዋን ሁሴን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጠላፊው አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ባረፈበት ወቅት ወደ አውሮፕላኑ ሳይገባ እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡
 
የጠለፋው ዓላማ ባይታወቅም ቢቢሲ በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ በአውሮፕላኑስጥ ካሉት የተወሰኑት ጥገኝነት ሳይጠይቁ እንደማይቀር ገልጿል፡፡ ተጠልፎ ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጠላፊ ረዳት ፓይለቱ እንደሆነ ታወቀ፡፡

 የቦይንግ አውሮፕላኑ ካፒቴን ወደ መጸዳጃ ቤት በሄደበት ወቅት አውሮፕላኑን የተቆጣጠረው ረዳት ፓይለቱ አውሮፕላኑን ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ ካሳረፈ በኋላ ከአውሮፕላኑ በመስኮት በገመድ ተንጠላጥሎ በመውጣት እጁን ለፖሊስ በመስጠት ጥገኝነት እንደጠየቀ ታውቋል፡፡ በትዊተር ማህበራዊ ገጽ ላይ በተለቀቀ የፓይለቱ ወይም የረዳት ፓይለቱ እንደሆነ በግልጽ ባልታወቀና ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ጋር በተደረገ የሬድዮ ግንኙነት ላይለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን እንደማንሰጥ ማረጋገጫ ወይም ጥገኝነት እንዲሰጠን እንጠይቃለንየሚል መልዕክት ተደምጧል፡፡

No comments:

Post a Comment