Thursday, February 13, 2014

አዳማ የተመሰረተችበትን አንድ መቶኛ ዓመት ልታከብር ነው

   አዳማ የተመሰረተችበትን አንድ መቶኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል ልታከብር ነው ።  የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ ዩሱፍ የአዳማ  የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የሚከበረው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሚጠናቀቅበት አመት ላይ በመሆኑ፥ለእቅዱ ስኬታማነት አስተዳድሩና ነዋሪው  በሙሉ አቅማቸው መረባረብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

      ከተማዋን ጽዱና አረንጓዴ በማድረግ የቱሪዝም ኮንፈረንስና የኢንዱስትሪ ማዕከልነትዋን ለማረጋገጥም ህብረተሰቡን ያሳተፈ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውንም ነው የገለፁት። የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው እንደገለጹት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን በማሳካትና የከተማዋን 100ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በድርብ ድልና ስኬት ለማጀብ ፤ ሁሉንም ያሳተፈ አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 

          አስተዳድሩም ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖረው በልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማገዝ እንዲሁም በጽዳትና አረንጓዴ ልማት ዙሪያ በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያለው። በዓሉ በሚቀጥለው አመት አመቱን በሙሉ እንደሚከበርም ነው የተመለከተው።
                                                                                                                                                              
                                                                           ምንጭ ፡-  ኤፍ.ቢ.ሲ 

No comments:

Post a Comment