ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትርፌ ፀጋዬ የቶኪዮ ማራቶንየቦታውን ክብረወሰን በመስበር ጭምር አሸነፈች ። ትርፌ
2፡22፡23 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የሴቶችን የማራቶን ውድድር በበላይነት የፈፀመችው።
ትርፌን በመከተልሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርሃኔ ዲባባ በ2፡22፡30 ሁለተኛ ስትወጣ ኬንያዊቷ ሉሲ ካቡ 2፡24፡16 ሶስተኛ ወጥታለች፡፡ አትሌቷ ይህን ውድድር በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ፥ ከሁለት ዓመት በፊት በሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አፀደ ሀብታሙ ተይዞ የቆየውን ሪከርድም አሻሽላለች።
የ29 አመቷ ትርፌ ጸጋዬ በ2008 የፖርቶ ማራቶንን በማሸነፍ የጀመረች ሲሆን በፓሪስ እና በዱባይ ማራቶንም ቀዳሚ መሆን ችላለች፡፡ የራሷን ፈጣን ሰአትም በርቀቱ በ2012 በበርሊን በ2፡21፡19 ማስመዝገቡዋ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያዊያን እና ኬንያውያን የበላይነት በተስተዋለበት የቶኪዮ ማራቶን በወንዶቹ ምድብ የ27 አመቱ ኬንያዊ ዲክሰን በ2ሰአት አምስት ደቂቃ 42 ሰከንድ አሸናፊ ሆኖ ሲገባ ኢትዮጵያዊው ታደሰ ቶላ በ2፡05፡57 ሁለተኛ ሆኖአል፣ ሶስተኛ ሳሚ ኪትዋራ በመሆን ገብቷል፡፡ ሁለቱ የአፍሪካ ሀገራት በወንዶቹ ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ በሴቶቹ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ወስደዋል::
ምንጭ : - www.iaaf.org
No comments:
Post a Comment