ህብረቱ በ22ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ የአፍሪካ የጤና ማዕከልን ለመገንባት መሪዎቹ በናይጀሪያ አቡጃ በተስማሙት መሰረት የአህጉሪቱን ታላቁ የጤና ማዕከል በአዲስ አበባ ይገነባል ፡፡
የጤና ማዕከሉ የምርምር፣የምክርና አፍሪካን የሚመለከቱ ማንኘውንም ጤና ነክ ጉዳይ በበላይነት የሚቆጣጠር ይሆናል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ጥር 23 ማመሻውን የተጠናቀቀ ሲሆን በመሪዎቹ የሁለት ቀንናት ቆይታም ከ2014 እስክ 2017 የሚዘልቅ የአፍሪካን የልማት ስትራቴጅክ እቅድ ተወያይተው አፅድቀዋል፡፡
መሪዎቹ በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት፣ በግጭት ቀጠናዎች፣ አፍሪካ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ያላትን ትስስር እንዲሁም በግብርናና በምግብ ዋስትና መክሯል፡፡ የቀጠዩ የአፍሪካ ህብረት 23ኛው የመሪዎች ጉባኤ ሃምሌ ወር ላይ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ይካሄዳል፡፡
No comments:
Post a Comment