Friday, February 7, 2014

በኢትዮጵያ ብቻ የሚበቅሉ የግብርና ምርቶች በአለም አእምሯዊ ንብረት ሊመዘገቡ ነው

   
    በኢትዮጵያ ብቻ የሚበቅሉ የግብርና ምርቶች በተለይም ጤፍ በአለም አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት እንዲመዘገብ የበኩሉን እንደሚወጣ የአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት አስታወቀ፡፡

   ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የአለም አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ሀላፊ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ የግብርና ምርቶች በአለም አእምሯዊ ንብረትፅህፈት ቤት መመዝገባቸው ለሀገሪቱ የግብርና ኢንዱስትሪ ሽግግር የጎላ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ በተለይም ምርቶቹን በአለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል፡፡
        
   የአለም አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ሀላፊ ፍራንሲስ ጌሪ በበኩላቸው ተቋማቸው ከምርቶች የምዝገባ ሂደት ባሻገር ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ጋር በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment