ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ ሀገሮች በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያኖቹ መሀመድ አማን፣ ህይወት አያሌውና ገንዝቤ ዲባባ ውድድራቸውን በቀዳሚነት አጠናቀዋል፡፡

በቤት ውስጥ ውድድር ሁለት ጊዜ ክብር ወሰን የሰበረችው የጥሩነሽ ዲባባ ታናሽ እህት ገንዘቤ ዲባባ ፣እንድ ጥሩነሽ ሁሉ የራሷን ታሪክ በዓለም የሩጫ መድረክ መስራት ቀጥላለች፡፡ ገንዘቤ ባለፈው ቅዳሜ በጀርመን የተካሄደውን የ1ሺህ 5 መቶ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር 3፡55፡17 በሆነ ሰዓት በመግባት የርቀቱን ክብር ወሰን በእጇ አስገብታለች፡፡
"በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ እርቀቱን ከዚህ ያነሰ ሰዓት በመግባት ክብር ወሰኑን ለመያዝ ጠንካራ ስራ እሰራለሁ ብላለች "ገንዘቤ ከውድድሩ በኋላ ለአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በሰጠችው ቃለ ምልልስ፡፡
ህይወት አያሌው በበኩሏ እሁድ በፈረንሳይ በተካሄደው አገር አቋራጭ ውድድር በድንቅ ብቃት ቀዳሚ ሆና ገብታለች፡፡ ህይወት በዓመቱ በጎዳና ላይ ያደረገቻቸውን ውድድሮች በሙሉ ማሸነፍ የቻለች ሲሆን የእሁዱ አሸናፊነት 6ኛዋ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment