Sunday, February 2, 2014

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ከምስራቅ አፍሪካ ለተውጣጡ ተማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ነው


 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ከምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት (ኢጋድ) የተወጣጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ በተቀናጀ የወንዞች ተፋሰስ ልማት አስተዳደር ላይ የድህረ ምረቃ ሰልጠና መስጠት ጀመረ። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ዘርፉ አስተባባሪ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር እያሱ ያዘው እንደገለጹት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ከምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት(ኢጋድ) ለተወጣጡ ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ማስተማር የጀመረው በኢጋድ በመመረጡ ነው።

   በተቀናጀ የወንዞች ተፋሰስ ልማት አስተዳደር የድህረ ምረቃ ትምህርቱ ዓላማ የተጀመረውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በማድረግ የውሃ አጠቃቀም፣ የመሬት ልማትና የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤን በማሻሻል የተቀናጀ የልማት አቅጣጫ በመከተል ምርትን በእጥፍ ለማሳደግ እንደሆነ ገልጸዋል።

      በትምህርት ዘርፉ ውሃ፣ መሬት፣ ስነ ህይወትና ደን በአንድ የተፋሰስ ልማት በማቀናጀት ከመነሻው እስከ ተጠቃሚዎች ልማት በአንድ ፍሰት በማስተዳደር የሃብት አጠቃቀምን ለመጪው ትውልድ በተገቢው መንገድ ለማስተላለፍ የትምህርት ዘርፉን ተመራጭ አድርጎታል ብለዋል።

     ትምህርቱ ምርትን በማሳደግ የህዝቡን ኑሮ በማሻሻል አከባቢ ሳይጎዳ ከአቅም በላይ የህዝብ መጨናነቅ ሳይፈጠር ያለውን ሃብት በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ የሚረዳ መሆኑንም  ዶክተር እያሱ አስታውቀዋል።

   የትምህርት ዘርፉ በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን የውሃ እጥረት፣ የመሬት ለምነት መቀነስና የህዝብ ቁጥር መጨመር የሚያስከትለውን የሃብት አለመመጣጠን በማቃለል በሃገሮች መካከል መልካም ጉርብትናና ወንድማማችነትን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ዶክተር እያሱ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment