Monday, August 26, 2013

ለ 40 ቀን 40 ለሊት እንጾማለን ብለው ሚስትን ለሞት ዳረጉ ልጆቹም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

ያለምንም እህል እና ውሃ ጾምን ለ 40 ቀን 40 ሌሊት እንጾማለን ብለው ጾማቸውን የጀመሩት የቤተሰብ አባላት ለከፍተኛ ጉዳት እና ለሞት መዳረጋቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ። በጎተራ ኮንደሚኒየም ውስጥ ይኖሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች በእምነታቸው መሰረት  ጾም ጸሎትን እያደረግን አምላክን በጸሎት እናስባለን በማለት ጾማቸውን ይጀምራሉ ።  ባል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ያለው  ሲሆን  ሚስት ደግሞ ከጂማ ዩኒቨርሲቲ በዶክትሬት ዲግሪ ተመረቃለች ። እነዚህ ባልና ሚስቶች  የ9 አመት እና የስድስት አመት ልጆችንም  አፍርተዋል ።

 ከምግብ እና ከውሃ ተለይተው ለልጆቻቸው ብቻ በጣም ጥቂት ምግብን በመያዝ  ቤታቸውን ዘግተው በፆም በፀሎት ለቀናቶች ሰንብተዋል ። ይህ ሂደት ለ25 ቀናት የተጓዘ ሲሆን ባለቤቷ እያበሰለ ለልጆቹ ከሚያቀርበው ምግብ ለራሱ በጥቂቱ የሚቀምስ ሲሆን ለባለቤቱ ሲሰጣት ግን ምንም አይነት ነገር መመገብ አለመቻሏን እና ምንም አያገባህም በማለት ምላሽ ታክል እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

 ሆኖም ግን 40ኛ ቀኑ ከመድረሱ አራት ቀን በፊት የእናቷ የአፍጠረንን መለወጥ ያየችው ህጻን ከወላጅ እናቷ ተለይታ  ከታናሽ እህቷ ጋር በሶፋ ላይ መተኛት መጀመሯን እና ከዚያም በመስኮት እራበን ድረሱልን እያለች ትጮሀለች ፡፡ ይህን የሰማች የጎረቤት ልጅ መጥታ በበር ቀዳዳ በተሰጣት ቁልፍ ከፍታ በመግባት ፣ሁለቱ ህጻናቶች በምግብ ጉዳት ምክንያት ከስተው የተገኙ ሲሆን ባል እራሳቸውን በመሳት በሆስፒታል በህክምና ክትትል ሲድኑ  ሚስትዬዋ ግን በህይወት ሊተርፉ አለመቻላቸውን ከአካባቢው ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ ፡፡  የቀበጡ ዕለት.......... ይባል የለ፡፡

No comments:

Post a Comment