Monday, August 26, 2013

በአዲስ አበባ 320 ሜትር ርዝመት ያለው ህንጻ ሊገነባ ነው

   

   ህንጻው በአዲስ አበባ ትልቁ ሲሆን ለሆቴል፣ ለቢሮ እና ለሱቅ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የሚገነባው ህንፃ 1 ሺህ ክፍሎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስተሮች መልካም አማራጮችን በማቅረብ እያበረታታ ሲሆን ለግንባታው የሚሆን ቦታ መስጠቱን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሊዩ ያንሊን አስታውቀዋል፡፡ ይሄው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጠውን ህንጻ ሰርቶ ለመጠናቀቅ 4 ዓመት እና 3 መቶ ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎም ተገምቷል፡፡


ህንጻውን የሚገነባውና የሚያስተዳድረው የቻይናው ድርጅት  በቻይና የሚያስተዳድራቸው ሶስት ሆቴሎች ስላሉትም ለግንባታው ብዙም እንደማይቸገር ነው የተገለጸው፡፡ የህንጻው ባለቤት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁዋንግሻን የሲሚንቶ ፋብሪካ በማቋቋም  ነበር የተሳተፈው ሲል የዘገበው ቻይና ዴይሊ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment