Thursday, August 8, 2013

ሻምበል አበበ ቢቂላ....

   
  አበበ በቂላ በወቅቱ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ በደብረብርሃን አውራጃ በቦነአ ምክትል ወረዳ ጃቶ ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወ/ ውድነሽ በነበሩ ነሐሴ 30 ቀን 1925 .. ተወለደ፡፡ እንደ አካባቢው የገበሬ ልጆች ሁሉ በልጅነቱ የፈረስ ጉግስ፣ የገና ጨዋታና ሩጫን ያዘወትር ነበር፡፡ በጣም ሯጭ ስለነበረጭልፊትየሚል ቅጽል ተሰጥቶታል፡፡

   1940 .. የንጉሠ ነገስቱ የክብር ዘበኛ የወታደር ቀጣሪ ቡድን ወደ ደብረብርሃን አውራጃ ሄዶ ስለነበረ በወረዳ ገዢውና በጭቃ ሹሙ አማካይነት ለወታደርነት ይበቃሉ የተባሉት ወጣቶች በጃቶ ቀበሌ ተሰበሰቡ፡፡ መራጩ ቡድን ብቁ ናቸው ያላቸውን ሰብስቦ 3 ሻለቃ ካምፕ አሳረፋቸው፡፡ ወጣት አበበ ቢቂላ ዕድሜው 15 ዓመት ስለነበረ ለወታደርነት ብቁ አይደሉም ተብለው ከተመለሱት አንዱ ነበር፡፡ አበበ ለአምስት ዓመታት ጃቶ ከቆየ በኋላ ወላጅ እናቱ ከአባቱ ተፋተው ወደ አዲስ አበባ መጥተው ስለነበረ ከእርሳቸው ጋር እየኖረ በወታደርነት ለመቀጠር ዕድሉን እንደገና ለመሞከር ወሰነ፡፡ ምኞቱ ተሳክቶለት ሚያዚያ 12 ቀን 1945 .. ተቀጠረ፡፡ ለስድስት ወራት የውትድርና ትምህርት ከተከታተለ በኋላ 5 ሻለቃ ምድብ ተደለደለ፡፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ ስፖርት እየተለማመደ ለስምንት ዓመታት ከቆየ በኋላ በጦር ኃይሎች ስፖርት ውድድር ተካፈለ፡፡ አበበ የማራቶን ርቀት ስለማያውቅና ሰዓትም ስላልነበረው ከሚገባው በላይ በመሮጥ ብዙ ጊዜ ወድቆ አረፋ መድፈቁን ተናግሯል፡፡

     በወቅቱ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በተገኙበትና በአዲስ አበባ ስታዲዮም በተደረገው የጦር ኃይሎች ውድድር አበበ በማራቶን አንደኛ ወጣ፡፡ ለዓመታት በዋሚ ቢራቱ ተይዞ የቆየውን ሪኮርድ በመስበር ከንጉሡ እጅ ሜዳሊያ፣ ትልቅ ዋንጫና ልዩ ሽልማት በማግኘቱ ስፖርቱን በእጅጉ አፈቀረ፡፡ በዘመኑ አበበ ሬዲዮ ስላልነበረውም የስፖርት ዜናዎችን ለመስማት ከቀጨኔ መድኃኔዓለም ጊዮርጊስ ወደሚገኘው የሕዝብ ሬዲዮ ግራማፎን ሂዶ ማዳመጥ ጀመረ፡፡ አበበ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት አሠልጣኝ ባያገኝም የሮም ኦሊምፒክ እንደተቃረበ አሠልጣኝ ኦኒ ኒካስተን በማግኘቱ ተስፋው ለመለመ፡፡  የልዑካን ቡድኑ አባለት ሐምሌ 27 ቀን 1952 ሮም ገብተው ስፖርተኞቹ 38 ቀናት አየሩን ከተለማመዱ በኋላ በማራቶን ተወዳደሩ፡፡ ጳጉሜ 5 ቀን 1952 .. 68 ታዋቂ የማራቶን ሯጮች ጋር አበበ በባዶ እግሩ ሩጦ 2 ሰዓት 15162 ሴኮንድ አንደኛ ወጣ፡፡

      
      ይሄኔ ዓለም ጉድ አለ፡፡ ኢትዮጵያ የት እንደሆነች የማይውቁ ሰዎች የዓለም ካርታን ማገላበጥ ጀመሩ፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አፍሪካም ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያና አዲስ ሪኮርድ አስመዘገበች፡፡ አበበ ከአሸነፈ በኋላ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስእኔ የዓለም ሻምፒዮን ነኝ እንጂ የኢትዮጵያ አንደኛ አይደለሁ፡፡ ለዚሁም ማስረጃ ከኔ የበለጠ ይሮጥ የነበረና በሕመም ምክንያት ወደ ሮም ሳይመጣ የቀረ ጓደኛዬ አለብሏል፡፡ በመቀጠልም “..እርግጥ ነው እኔ ወደ ሮም ስመጣ አበበ አሸንፎ ይመጣል ብሎ ያሰበ አንድም ሰው አልነበረም፡፡ እኔ ግን ከቤቴ ስወጣ አሸናፊ ሆኜ እንጂ ተሸንፌ እመለሳለሁ የሚል እምነት አልነበረኝምበማለት በራሱ ላይ ምን ያህል እምነት እንደነበረው ተናግሯል፡፡ ስለተደረገለት ማበረታቻ ሲናገር፣እኔ አሸንፌ ስገባ በነበረው ጭብጨባና ሁካታ እንኳንስ እኔ ነፍስ ኖሮኝ የምሮጠው ልቅርና ሙታኖች ምን ተፈጠረ ብለው ይነሳሉ፣ ይነቃሉ ብዬ ሰግቼ ነበርብሏል፡፡

   የማራቶኁ ጀግና ከሮም እንደተመለሰ ምክትል የአስር አለቃነት ማዕረግ ስለተሰጠው ቅር ቢሰኝም፣ ከስፖርት አፍቃሪው ሕዝብ የተደረገለት አቀባበል ውድድሩን በሞራል እንዲቀጥል ረድቶታል፡፡እንዴት ይረሱታል የአበበን ዝና፣ መሐንዲስ ይመስል ሲቀይስ ጐዳናተብሎ ተገጥሞለታል፡፡ አበበ በ1953 ዓ.ም. በአራት የማራቶን ኢንተርናሽናል ውድድሮችን ማሸነፉ በዝና ላይ ዝና አጐናፀፈው፡፡ በ1954 በተለያዩ አገሮች በግማሽና ሙሉ ማራቶን ስምንት ጊዜ አሸነፈ፡፡ በ1955 ዓ.ም. በ7፣12፣20 ኪሎ ሜትርና ማራቶን በድል ላይ ድል በመጐናፀፉ ዝናው ይበልጥ ናኘ፡፡
    
     አበበ ቢቂላ 1957 .. በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመካፈል በጥሩ ዝግጅት ላይ እንዳለ በድንገት በትርፍ አንጀት ህመም ስለተያዘ ኦፕራሲዮን ተደረገ፡፡ የቀዶ ጥገና ሕክምና በተደረገለት 47 ቀናት በቶኪዮው ኦሊምፒክ ማራቶን ተካፍሎ 78 አገሮች ተወዳዳሪዎች 2 ሰዓት 12112 ሴኮንድ አንደኛ ከመሆኑም በላይ የማራቶንን ክብረ ወሰን ሰበረ፡፡ በዚህ ውጤት የተደሰቱት አፄ ኃይለሥላሴ የሙሉ አለቃነት ማዕረግ ሰጡት፡፡ 

  አበበ በኦሊምፒክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አገሮች ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጐ 26 ጊዜያት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያዎችንና ከፍተኛ ዋንጫዎችን ተሸልሟል፡፡ከብዙ በጥቂቱ በአቴንስ፣ በበርሊን፣ በስዊድን፣ ከኮፐንሃገን፣ በቦክስቼ፣ በኦሳካ፣ በቦስተን፣ በብራዚል፣ በሳስቶ ፓስቲንያ፣ በማንቺ፣ በስፓኝ፣ በሴኦል ወዘተ የተጐናፀፋቸው ድሎች ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ናቸው፡፡ የመቶ አለቃ አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ማራቶን ሁለት ጊዜ በማሸነፍ አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገቡ በሜክሲኮው ኦሊምፒክም ያሸንፋል ተብሎ ሲጠበቅ እስከ 15ኛው ኪሎ ሜትር ከመራ በኋላ በደረሰበት የደም ስር መሸማቀቅ አቋርጦ ቢወጣም ሻምበል ማሞ ወልዴ በማሸነፉ አገራችን በተከታታይ በሶስት ኦሊምፒኮች በማራቶን በማሸነፍ እስከ ዛሬ ድረስ ብቸኛዋ አገር ሆናለች፡፡ ለአበበም የሻምበልነት ማዕረግ ተሰጠው፡፡
    
    ዳሩ ግን የአበበ ዝና ሳይቀዘቅዝ አሳዛኝ አደጋ ደረሰበት፡፡ መጋቢት 15 ቀን 1961 .. ከአዲስ አበባ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደረሰበት የመኪና አደጋ ክፉኛ ተጐዳ፡፡ በክብር ዘበኛ ሆስፒታል ለአምስት ቀናት ከታከመ በኋላ በንጐሱ ፈቃድ ወደ እንግሊዝ ለሕክምና ተልኮ ለስምንት ወራት ከፍተኛ ሕክምና ቢደረግለትም ሊድን ባለመቻሉ የአካል ጉዳተኛ ሆነ፡፡ በሁኔታው የዓለም ሕዝብ አዘነለት፡፡ 4400 የገና ርዶችም ከዓለም ዙሪያ ደረሱት፡፡ ንጉሠ ነግስቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ ሄደው ሲጠይቁት፣ ፕሬዚዳንት ኒክሰንና ፕሬዚዳንት ጆንሰን ደግሞ በቴሌግራም አጽናንተውታል፡፡

   ሻምበል አበበ የአካል ጉዳተኛ ከሆነም በኋላ በተለያዩ ኢንተርናሽናል ውድድሮች ተካፍሏል፡፡ 1963 .. በእንግሊዚ አገር በተካሄደው የቀስት ውድድር ተካፍሎ ልዩ ሽልማት አግኝቷል፡፡ በዚሁ ዓመት በኖርዌይ በተደረገው 25 ኪሎ ሜትር የጋሪ ውድድር አንደኛ ከመውጣቱ በተጨማሪ በሶስተኛው ቀን 120 ኪሎ ሜትር አሸንፏል፡፡ የሻምበል አበበ ጤንነት በየጊዜው እየተናጋ ሄዶ ጥቅምት 15 ቀን 1966 .. ከጠዋቱ በሁለት ሰዓት 45 ላይ አርፎ ጥቅምት 16 ቀን 1966 .. በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ተቀበረ፡፡
     
    ሻምበል አበበ በባዶ እግሩ ሮጦ በሮም ኦሊምፒክ የነበረውን ሪኮርድ በማሻሻሉ፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ቀዶ ጥገና ተደርጐለት ብዙም ሳይቆይ ከማሸነፉም ሌላ የራሱን ሪኮርድ ራሱ በማሻሻሉ አበበና ኦሊምፒክ በወርቅ ቀለም የተጻፈ የታሪክ ቁርኝት አላቸው፡፡


No comments:

Post a Comment