Saturday, August 10, 2013

ከ14ኛዉ የአለም ሻምፒዮና ምን እንጠብቅ!




ኢትዮጵያ በአለም ሻምፒዮናዉ 19 ወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡ ከነዚህ ወርቆች ዉስጥ ዘጠኙ የተገኙት 10000 ሜትር ወንዶች ነዉ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ኃይሌ /ስላሴ በርቀቱ ወርቅ ካሰመዘገበ በኋላ ላለፉት 20 አመታት ከኤድመንተኑ አለም ሻምፒዮና ዉጭ ኢትዮጵያ 10 000 ሜትር ወርቅ ያጣችበት ጊዜ የለም፡፡

ኃይሌ- ከስቱትጋርት እስከ ሲቪያ 4ወርቆች
ቀነኒሳ - ከሴንት ዴኒስ እስከ በርሊን 4ወርቆች
ኢብራሂም - ዴጉ 1 ወርቅ

   በሞስኮው 14 የአለም ሻምፕዮና ምሽት 11 ሰአት 55 በተካሄደው 10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ኢብራሂም ጄይላን 27:22:23 ደቂቃ  ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል ዛሬ ረፋድ 5 ሰአት ላይ በተካሄደው የወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያም ኢትዮጵያዊው መሃመድ አማን አንደኛ በመውጣት ማጣሪያውን በቀላሉ ማለፍ ችሏል። በተመሳሳይ 10 ሰአት 20 ላይ  በተካሄደው የሴቶች 3 ሺህ መሰናክል የማጣሪያ ውድድር ሶፊያ አሰፋ እቴነሽ ዲሮ እና  ህይወት አያሌው ለፍጻሜ አልፈዋል።

No comments:

Post a Comment