Monday, May 13, 2013

የቤት ፈላጊዎች መስፈርትና የምዝገባ መመሪያ ይፋ ተደረገ


i       ግንቦት 3/2005  የአዲስ አበባ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ  የ 40 በ 60 ፣ የ 10 በ90 እና 20 በ80 የጋራ መኖሪያ  ቤት ፈላጊዎች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታና የምዝገባ ስነ ስርአት ይፋ አደረገ ፡፡
      በዚህም መሰረት የ 10 በ 90 እና የ 20 በ 80  ምዝገባ ከሰኔ 3 እስከ 21 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት በሁሉም ወረዳዎች ይደረጋል ፡፡
      የ 40 በ 60 ምዝገባ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በተመረጡ ቅርንጫፎች  ከሀምሌ 5 እስከ 17  የሚካሄድ ሲሆን ፥ በማህበር ለሚደራጁ ደግሞ ምዝገባው  ከ ሀምሌ 15 እስከ 30 የሚካሄድ ይሆናል ፡፡
ለመንግስት ሰራተኞች ደግሞ በተለየ ሁኔታ  117 ኛ መመዝገቢያ ቦታ ተዘጋጅቶ ምዝገባው ለብቻ የሚካሄድ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ አሳውቋል ፡፡
ለምዝገባ ብቁ ለመሆንም በቢሮው የሚከተሉት መስፈርቶች ተቀምጠዋል ፡፡
* እድሜው/ዋ ከ 18 አመት በላይ የሆነ
* በከተማው ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ አመታት የኖረና እየኖረ ያለ።
* የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ አመታት በስራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ  የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ፥ ማስረጃው ቦታውን ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ካቀረበ ብቁ ይሆናል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈግ የቁጠባ መጠን ደግሞ ይሄ ነው ብሏል ቢሮው ፥
ለ 40 በ 60
ለባለ 3 መኝታ ቤት  ብር 2453
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 1275
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  1053
ለነባር 20 በ 80
ከምዝገባ ቀን ጀምሮ በየወሩ በተከታታይ 5 አመት መቆጠብ ይኖርበታል
ለ ባለ 3 መኝታ ቤት ብር 685
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 561
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 274
ለስቲዲዮ መኝታ ቤት ብር 151
በአዲስ  20 በ 80
ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 489
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 401
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  196
ለ10 በ 90

የመጀመሪያ የቁጠባ መጠን ብር 187 ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሳይቋረጥ በተከታታይ  ለ 2 አመታት መቆጠብ ይኖርበታል

No comments:

Post a Comment