ሌሊሳ ዴሲሳ ያደረገው የስፖርትን የሰላም ተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው -ጆን ኬሪ
የቦስተን ማራቶንን ያሸነፈው ሌሊሳ ዴሲሳ በቦስተን ማራቶን የተሸለመውን የወርቅ ሜዳሊያ በውድድሩ ማጠናቀቂያ ወቅት በደረሰው የቦንብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች በማስታወሻነት አበርክቷል፡፡ አትሌቱ ዛሬ ግንቦት 18/2005 በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በመገኘት ለሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ሜዳሊያዉን አስረክቧል፡፡
ጆን ኬሪ አትሌቱ ያበረከተው የማስታወሻ ስጦታ የስፖርትን የሰላም ተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው በማለት አመስግነዋል።
“እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ይህንን በሰማሁ ጊዜ ደስታዬ ደብዝዟል” ያለው ሌሊሳ የቦስተን ህዝብ ለሱ ደስታ ያበረከተለትን ሜዳሊያ ለተጎጂዎች ለመስጠት መወሰኑን ገልጿል።
ጆን ኬሪ አትሌቱ ያበረከተው የማስታወሻ ስጦታ የስፖርትን የሰላም ተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው በማለት አመስግነዋል።
“እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ይህንን በሰማሁ ጊዜ ደስታዬ ደብዝዟል” ያለው ሌሊሳ የቦስተን ህዝብ ለሱ ደስታ ያበረከተለትን ሜዳሊያ ለተጎጂዎች ለመስጠት መወሰኑን ገልጿል።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ይህ ውጣት አትሌት አሁን እዚህ የተገኘው በቦስትን ማራቶን ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ያገኘውን ሜዳሊያ በማስታወሻነት ለመስጠት ነው። እንደዚህ አይነት ልዩ ክንዋኔ የሚፈፅሙ ደግሞ ጥቂቶች ናቸው፡፡ በወቅቱ በተከሰተው ድርጊት በማዘኑ የፈፀመው አርያነት ያለው ድርጊት እኔንም አስደምሞኛል፡፡ በጣም ላመሰግነው እወዳለሁ” ብለዋል። የቦስተንን ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያሸንፍም ተስፋ አድርጋለሁ ብሏል ።
No comments:
Post a Comment