Monday, May 27, 2013

    የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ይፋ ሆነ

d     የ10 /90 እና የ20/ 80 የቤቶች ፕሮግራም ምዝገባን ለማካሄድ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ ፡፡
ኤጀንሲዉ በነዚህ የቤት ፕሮግራሞች የመንግስት ሰራተኞች የተሻለ ጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻቻለሁ ብሏል፡፡4 ሺህ ሙያተኞችና የስራ ሃላፊዎች ምዝገባውን ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስልጠና  በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ነው የገለፀው ፡፡

      የቤት ፈላጊዎች መመዝገብ የሚችሉት ካሉት የቤት ፕሮግራሞች በአንዱ ብቻ  በመሆኑ ከወዲሁ ወስነው እራሳቸውን እንዲያዘጋጁና ፥ ምዝገባው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ብቻ የሚካሄድ በመሆኑ የቤት ፈላጊዎች በእድሉ  እንዲጠቀሙ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡ከሚፈልጉት የቤት መርሃ ግብር ፣ የቤት ዓይነትና  ዋጋ  ከወዲሁ ወስነው መዘጋጀት አለባቸው በማለት ከገንዛቤ ሊያስገቧቸው የሚችሏቸውን መነሻ  የቤቶች ዋጋን  ዝርዝር  ይፋ አድርጓል ።

  የ10/90 መርሃ ግብር አጠቃላይ የቤት ዋጋ 38ሺህ ብር

          የ20/80 መርሃ ግብር
ባለ አንድ መኝታ 126 ሺህ 721 ብር
ባለ 2 መኝታ 224 ሺህ ብር
ባለ 3 መኝታ 304 ሺህ 215ብር

        ለነባር 20/80
ስቱዲዮ 61 ሺህ ብር
የ40/60 መርሃ ግብር
ባለ 1 መኝታ 162ሺህ 645 ብር
ባለ 2 መኝታ 250 ሺህ ብር
ባለ 3 መኝታ 386 ሺህ 400ብር

     የማህበራት ቤት
ባለ 1 መኝታ 210 ሺህ ብር
ባለ 2 መኝታ 280 ሺህ ብር ፣ ባለ 3 መኝታ  385 ሺህ ብር
የ10/90 እና የ20/80 ቤቶች ምዝገባ  ከሰኔ  3 አስከ 21 2005  ዓመተ  ምህረት  ድረስ እንደሚካሄድ ኤጀንሲው ማስታወቁ ይታወሳል ።

No comments:

Post a Comment