Wednesday, June 4, 2014

የፍጥነት መንገዶች በክፍያ የሚተዳደሩበት አዋጅ ፀደቀ


   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድና በቀጣይ የሚገነቡ የፍጥነት መንገዶች በክፍያ ስርአት የሚተዳደሩበትን አዋጅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ በተለይ የፍጥነት መንገዶች ከፍተኛ የግንባታ ወጪ የሚይጠይቁና ካላቸው ልዩ ባህሪ ጋር በተያያዘ ነው በክፍያ ስርአት እንዲመሩ የሚያስችለውን አዋጅ ያፀደቀው፡፡

  አዋጁ በክፍያ የፍጥነት መንገድ የሚተላለፉ ተሽከርካሪዎች ተመጣጣኝ ክፍያ በማስከፈል እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ ሲሆን፥ የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ የመንገድ ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተጠቅሷል። በፍጥነት መንገዱ ላይ 30 ደቂቃ የሚቆይ ተሽከርካሪ 100 ብር እንደሚቀጣና የፍጥነት መንገዱን የሚያቋርጥ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካልም እንደሚቀጣ አዋጁ ይገልፃል፡፡


  ምክር ቤቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የፓን አፍሪካ ኤጀንሲ ማቋቋሚያን ኮንቬንሽንም በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፥ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችንም ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።
                                                                                                                                ምንጭ ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment