Monday, June 2, 2014

ኢትዮጵያ በቡርንዲ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስ እርዳታ አደረገች

    ኢትዮያ በቅርቡ በቡርንዲ ዋና ከተማ ቡጅምብራ አከባቢ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስ እርዳታ አደረገች፡፡የቁሳቁስ እርዳታው ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ኢትዮያ ለቡርንዲ የሰጠችው የቁሳቁስ እርዳታ በቡጅንብራ አከባቢ ላሉ የጎርፍ ተጠቂዎች መልሶ ማቋቋምያ የሚውል ነው፡፡
  በቅርቡ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከ5 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖርያቸው መፈናቀላቸው ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ የዕርዳታ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡በዚህም ኢትዮያ ለቡርንዲ በቁሳቁስ ለመርዳት ቃል በገባችው መሰረት 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት 50 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ 5 ሺህ ብርድ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶች አበርክታለች፡፡ቁሳቁሶቹን የማጓጓዝ ስራው የኢፌዴሪ አየር ሀይል እያከናወነው ነው፡፡
 በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ዳይሬክቶር አቶ ገብረስላሴ ገብረእግዚአብሄር እንዳሉት ኢትዮያ ለቡርንዲ የሰጠችው እርዳታ በሁለቱ ሀገራት ያለው ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና የአዳማ ማእከላዊ ሎጂስቲክስ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አበበ በበኩላቸው ኢትዮያ ለአስቸኳይ እርዳታ የሚሆን የቁሳቁስ ክምችቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተናግረዋል፡፡    
                                                       ምንጭ ፡- ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment