Thursday, June 5, 2014

የፎርብስ መፅሄት በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በንግድ ዘርፍ ውጤታማ ያላቸውን አስር ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ አደረገ

የፎርብስ መፅሄት በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በንግድ ዘርፍ ውጤታማ ያላቸውን አስር ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ አድርጓል። ፎርብስ በዋነኛነት የቴክኖሎጂ ፈጠራ አጠቃቀም እና ገበያ ተኮር የንግድ እንቅስቃሴን በመመዘኛነት በመጠቀም ነው ዝርዝሩን ይፋ ያደረገው። 

 
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ  ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያ  ኬንያ  ግብፅ እንዲሁም ዚምባቡዌየሚገኙ ባለሀብቶችን በዚሁ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።

  ኢትዮጵያዊው የሚድሮክ ግሩፕ እና ደርባ ስሚንቶ መስራች ሼክ ሞሃመድ አሊ አላሙዲን በዚህ ዝርዝር ውስጥ በሶስተኝነት ተቀምጠዋል።ሚድሮክ ግሮፕ በዋናነት በወርቅ ማዕድን በግብርና በስሚንቶ እና በብረታ ብረት ምርት ላይ በመሰማራት ውጤታማ መሆን እንደቻለ ተጠቅሷል።

  በተጨማሪም በቴሌኮምንኬሽን ዘርፍ የተሰማሩት የሱዳኑ ኢብራሂም 74 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ የንግድ ኢንቨስትመንት ተቋም መስራች አለን ግሬይ ናይጄሪያዊው የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ደቡብ አፍሪካዊው የቢድቬስት ግሩፕ መስራች በመሆን 100, 000 ዜጎች የእንጀራ በር የከፈተው ብራያን ጆፌ ዋና ዋናዎቹ ናቸው

No comments:

Post a Comment