Wednesday, June 18, 2014

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አዲስ ክብረ ወሰን ያዘች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ53ኛው የኦስትራቫ ጎልደን ስፓይክ ውድድር ላይ በ2 ሺ ሜትር የአፍሪካን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች። የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ባዘጋጀው በዚህ ውድድር ላይ ሶስት የተለያዩ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ለማሻሻል ቢሞከርም ሳይሳኩ ቀርተዋል።
 ይሻሻላሉ ተብለው ከተጠበቁ ሶስቱ የዓለም ክብረ ወሰኖች አንዱ የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ የ2 ሺህ ሜትር ውድድር ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ባይሳካም አትሌቷ የአፍሪካ ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን ችላለች። ገንዘቤ በውድድሯ እስከ ግማሽ ርቀት የፈጀባት ሰዓት የዓለምን ክብረ ወሰን ለማሻሻል እንደሚያስችላት ቢገመትም የመጨረሻው 9 መቶ ሜትር ብቻዋን መሮጧ የዓለምን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ሳትችል ቀርታለች። በመሆኑም አትሌት ገንዘቤ ከ20 ዓመት በፊት በርቀቱ ተያዞን ከነበረው የዓለም ከብረ ወሰን ሰዓት በ2 ሰከንድ ዘግይታ ገብታለች።
   ከ20 ዓመት በፊት የ2 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በ5፡25.36 በሆነ ሰዓት በሶኒያ ሱሊቫን የተያዘ ሲሆን ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን 5፡27.36 በሆነ ሰዓት መግባት ችላለች። ይህም ሰዓት አትሌት ገንዘቤ ዲባባን በአፍሪካ የርቀቱ አዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል።

No comments:

Post a Comment