Monday, June 2, 2014

የኢትዮጵያ የህዋ ምርምር ቴለስኮፖች የሙከራ ስራቸውን ጀመሩ::

ኢትዮጵያ በእንጦጦ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ማሰልጠኛ ማዕከል ያስተከለቻቸው ሁለት የህዋ ምርምር ቴለስኮፖች የሙከራ ስራ መጀመራቸው ተገለፀ፡፡የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ እንደተናገሩት የተተከሉት ቴሌስኮፖች በኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ምርምር ተወዳዳሪ እንድትሆንና መረጃ እንድታሰባስብ የሚያግዙ ናቸው፡፡


ከጀርመኑ አስቴልኮ ኩባንያ በሁለት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ዩሮ የተገዙት ቴሌስኮፖች ሀገሪቱን ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ በአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል፡፡ የመሳሪያዎቹ መተከል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጭምር በምርምርና ስርፀት ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ የሀገሪቱን ገፅታ በመቀየርና  ጎብኝዎችን ለመሳብ ያለው አስተዋፅኦ የላቀ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment