Monday, June 23, 2014

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ትናንት በድምቀት ዋንጫውን ተረከበ።



  በ2006 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዋቂዎችና በታዳጊዮች በጥምር ሻምፒዮን መሆን የቻለው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ትናንት በድምቀት ዋንጫውን ተረክቧል። ስድስት ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮን መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ 11 ጊዜ ሻምፒዮን የሆነበትን የክብር ዘውድ የደፋው፥ ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲዮም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 0 በመርታት ነው፡፡ 
  ሻምፒዮኖቹ የሊጉን የዋንጫ ሽልማት ከዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተክለብርሃን እጅ ተቀብለዋልየቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ 1 መቶ 50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

 የሊጉ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ያጠናቀቀው ኡመድ ኡክሪ ኮከብ ግባ አግቢና ኮከብ ተጨዋች የሚለውን ደርብ ክብር አግኝቷል፡፡

 ኡመድ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ በመመረጡ የዋንጫ እና 10 ሺህ ብር ሽልማት አግኝቷል፡፡በ2006 የውድድር ዘመን በስፖርታዊ ጨዋነትን ፍጹም ምርጥ ቡድን በአዋቂዎች ሙገር ሲሚንቶ፣ በታዳጊዮች ኢትዮጵያ ቡና ተብለዋል፡፡

   ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ የዓመቱ ምርጥ ዋና ዳኛ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የዓመቱ ኮከብ አሰልጣኝነት ክብርን የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሬኒ ፎለር ሲቀዳጅ፥ ሮበርቶ ዶንካራ ደግሞ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ ተመርጧል። 11 ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ የጎል ሪከርዱንም አሻሽሏል፡፡

No comments:

Post a Comment