Monday, June 2, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 30 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው


 በመጪው ሰኔ ወር የኢትዮጵያ አየር መንገድ 30 የኤር ባስ ወይም የቦይንግ ጀት አውሮፕላኖችን ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ለመግዛት የሚያስችለውን ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አስታወቀ፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የአለም አቀፉ የአየር መንገዶች ጉባኤ እየተካሄደበት ባለው በኳታር ዶሃ ለሮይተርስ እንደተናገሩት አየር መንገዱ በቀጣይ የወጠነውን የማስፋፊያ እቅድ ለማሳካት ነው አውሮችላኖቹን ከኤር ባስ ወይም ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች መግዛት የሚያችለውን ውሳኔ ያሳልፋል፡፡ አየር መንገዱ ኤር ባስ 320 እና ቦይንግ 737 ከተባሉት ሁለት አይነት የአውሮፕላን ሞዴሎችን የተሻለውን ለመግዛት ሲያጠና መቆየቱን አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡አሁን ባለው ዝቅተኛ ዋጋ የአውሮፕላኖቹ ግዥ 3 ቢሊዮን ዶላር  ይደርሳልም ብለዋል፡፡ አየር መንገዱ እስካሁን ሙሉ ለሙሉ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ይዞ ነው አለም አቀፍ የበረራ አድማሱን እያሰፋ ያለው፡፡ 
  አዲስ የሚገዛቸው 30 አውሮፕላኖች እስከ 2025 እ.ኤ.አ አሁን ያለውን የአውሮፕላኖች ቁጥር ወደ 112 ለማድረስ ያስችለዋልም ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው፡፡ በዚህም አየር መንገዱ የመዳረሻ መስመሩን 92 የሚያደርስ ሲሆን ይህም ከ18 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የማመላለስ ራእዩን እውን ለማድረግ ያስችለዋል ተብሏል ፡፡
                                                ምንጭ፣ ሮዎይተርስ

No comments:

Post a Comment