Tuesday, June 3, 2014

ትውልደ ኢትዮጵያዊው በኋይት ሃውስ የሳይንስ አውደ ርዕይ ላይ ዕውቅና ተሰጠው

  
  በየአመቱ በኋይት ሃውስ የሳይንስ አውደ ርዕይ ይካሄዳል፡፡ በኤግዝቢዥኑ ላይ የተሻለ ፈጠራ ያላቸው ተማሪዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡በዘንድሮው ዝግጅት ላይ በአዲስ አበባ በእግረኞች ላይ የሚከሰተውን የተሽከርካሪ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የአደጋ መልዕክት የሚስተላልፍ መሳሪያ የሰሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፈለገ ገብሩና ባልደረባው ካረን ፋን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በተገኙበት እውቅና ተሰጧቸዋል፡፡
  "ኢትዮጵያ  ከፍተኛ የመኪና አደጋ ከሚደርስባቸው ሀገሮች አንዷናት፡፡ ፈለገና ካረን የሰሩት መሳሪያ ለአሽከርካሪዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሲሆን እግረኞችም በቀላሉ መንገድ እንዲያቋርጡ የሚያግዝ ነው፡፡ በፀሐይ ሃይል የሚሰራው መሳሪያ የመኪኖችን ፍጥነት ከግምት በማስገባት ለእግረኞች መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡" ሲልየኋይት ሃውስ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
  "በአውደ ርዕዩ ላይ ዝግጅት ለማቅረብ መጋበዝ በራሱ ለነዚህ ተማሪዎች ክብር ነው፡፡ በፈለገ፣ በካረንና በሌሎችም ተማሪዎች ላይ ያለው ለፈጠራ ያለ ፍቅርና ቁርጠኝነት በአርአያነት የሚወሰድና ሌሎቸንም የሚነሳሳ ነው፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ያላቸውን ዕውቀት በተግባር በማዋል በትምህርት ሊገኝ የሚችለውን ዕውቀት ያሳዩ ናቸው" ሲሉ የፈጠራ ትምህርት ሃላፊ የሆኑት ሌይ ኢስታበሩክ ገልጸዋል፡፡ተማሪ ፈለገ የ18 አመት ወጣት ሲሆን ማሳቹሴት የሚገኘውን ኒውተን ኖርዝ ትምህርት ቤት በመወከል ነው በመድረኩ ላይ የቀረበው፡፡ 

No comments:

Post a Comment