Wednesday, June 4, 2014

ለ2007 ዓ.ም ከ 178 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተረቀቀ


  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 27/ 2006 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ 2007 የፌዴራል መንግሥት በጀት 178 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ።በጀቱ እንዲፀድቅም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል  በጀቱ 2006 በጀት አንጻር ሲታይ 15 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ አለው ከተያዘው አጠቃላይ በጀት ለፌዴራል መንግሥት መደበኛ ወጪ 45 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ ደግሞ 66 ነጥብ 9 ቢሊዮን በድምሩ 112 ቢሊዮን የተመደበ ሲሆን፤ ለክልሎች ድጋፍ 51 ነጥብ 5 ቢሊዮን እና ለምዕተ ዓመቱ ግቦች ማስፈፀሚያ 15 ቢሊዮን ተመድቧል፡፡ 

  ለበጀቱ ዝግጅት ቀደም ሲል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የአራት አመት የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ በመነሻነት የተወሰደ ሲሆን፤ የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት በሚደግፍ መልኩም የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል ፡፡

  በአጠቃላይ የበጀት ዝግጅቱ ያለፉትን ዓመታት የመንግስት ገቢና ወጪ አፈፀፃም፣ የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት መሠረት ያደረገና የፕሮግራም በጀት ስርዓትን የተከተለ ነውም ተብሏል ፡፡  ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ አካላት የመንግሥት በጀትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቁጠባና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ በማዋል የተጀመረውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራና የአገሪቷን የህዳሴ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ እንደሆነ በመስማማት 2007 በጀት ዓመት የቀረበው በጀት ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ አስተላልፏል፡፡ 
                                                   
                                                   ምንጭ ኢዜአ
                                                     

No comments:

Post a Comment