Thursday, July 10, 2014

የዩኒሴፍ አምባሳደሯ ሐና ጎዲፋ ለልጃገረዶች ትምህርት ተኩረት ሊሰጠው ይገባል አለች፡፡


የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አምባሳደር ተብላ የተሰየመችው 16 ዓመቷ ሐና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚሊየን የሚቆጠሩ የትምህርት ዕድል ሳያገኙ የሚቀሩ ልጃገረዶች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የሚያስችል ተጨባጭ ስልት ሊነድፍ ይገባዋል ስትል ተናገረች፡፡



 በ15 ዓመቷ የዩኔስኮ አምባሳደር ተብላ የተሰየመችው ሐና ከኢትዮጵያውያን ወላጆች ካናዳ ውስጥ ተወልዳ ያደገችና 7 ዓመቷ አንስቶ በተሰማራችበት ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁሶች የማሰባሰብ ተግባሯ ትታወቃለች፡፡


  ሐና ባቋቋመችው የእርሳስ ተራራ ፕሮጀክት ስር ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች 500 000 በላይ የትምህርት መርጃ የጽሕፈት መሳሪያዎችን አከፋፍላለች፡፡ ሐና አሁን ላይ ደግሞ እቅዷን ሰፋ አድርጋ በቅርቡ በኢትዮጵያ ለተቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች መጽሐፍት እንዲሁም የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ወደ ማሰባሰቡ አዘንብላለች፡፡

No comments:

Post a Comment