Monday, July 14, 2014

ታዋቂው የወግ ፀሐፊ መስፍን ሀብተማሪያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ


  ጋዜጠኛ ደራሲና አርታኢ መስፍን ሀብተማሪያም ሐምሌ 6 ቀን 2006 . ከምሽቱ 345 ሰዓት ላይ አርፏል፡፡ ነገ - ሐምሌ 8 ከቀኑ 600 ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ - ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል፡፡

   መስፍን /ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ .. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለደ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በሞጆ /ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት /ቤት አጠናቋል። የከፍተኛ ትምህርቱንም በአ.. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በቢ. ዲግሪ ተመርቋል፡፡ በተጨማሪም ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ካናዳ በፈጠራ ድርሰቶች አጻጻፍ ኤም.. ዲግሪ ኤም.ኤፍ. ተቀብሏል፡፡ ሞጆ ከተማ የተወለደው ተወዳጁ የወግ ፀሀፊ ባደረበት ህመም ነው ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም የተለየው፡፡ በኡጋንዳ የሰላም ማስከበር ጊዜ ለስራ ከዓመታት በፊት አብሮ ሄዶ የነበረው መስፍን ኡጋንዳ የጀመረው ህመም ያዝ ለቀቅ ሲያደርገው መቆየቱን አለማየሁ ገላጋይ ይገልፃል፡፡ በህክምና ሲረዳ ቆይቶም ነበር፡፡

   መስፍን ሀብተ ማሪያም በደማም ብዕሩ በተለይ በወግ ጽሁፎቹ የሚታወቀው አንጋፋው ደራሲ The rich man and the singer (በእንግሊዝኛ)፣የቡና ቤት ስዕሎች ፣አባደፋርና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች፣ አውዳመት እና የሌሊት ድምፃች የተሰኙ ጣፋጭ ወጎችን አብርክቷል፡፡ እንዲሁም ‹‹አዜብ›› የተሰኘ የአጫጭር ልቦለድ ስራዎችን የያዘ መፅሀፍም ለህትመት አብቅቷል፡፡ 

  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረው መስፍን ሀብማሪያም /ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋውን የመሳሰሉ ምሁራንን አስተምሯል፡፡ ለረጅም ዘመናትም በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ውስጥ በአርታኢነት አገልግሏል፡፡ በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት በአርታኢነት የሠራው መስፍን ሀብተማርያም በኢትዮጵያ ሬዲዮ በተረካቸው የወግ ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡ 

  ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም ከኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር አስተርጓሚ በመሆን ወደ ኡጋንዳ አቅንቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለረዥም ጊዜ መታመሙን ወዳጆቹ ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን ባሉ እጅግ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ ሥራዎቹን ለአሥርት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ ጋዜጠኛ ደራሲና አርታኢ መስፍን ሐብተማርያም ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነበር፡፡

 ለደማሙ ብዕረኛ ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን እያልኩ፤ ለዘመድ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment