በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ላለችው የአዳማ ከተማ በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ቴክኒካዊ ድጋፍና በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ አዲስ ማስተር ፕላን ሊዘጋጅላት መሆኑ ታውቋል፡፡በአዲሱ ማስተር ፕላን ከተማዋ የመኖሪያ፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ዞንና ሌሎችም እንደሚኖሯት ተገልጿል፡፡
ከአዲስ አበባ በ98 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምትገኘው አዳማ እ.አ.አ በ1915 የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ዝርጋታን ተከትሎ እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ በ136.6 ስክዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈችው አዳማ 300,000 ህዝብ ይኖርባታል፡፡
ምንጭ ፡
- ድሬ ቲዩብ
No comments:
Post a Comment