Saturday, July 12, 2014

አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን አስመረቀ።


 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ሀምሌ 5 ቀን 2006 . የምረቃ ስነ ስርአቱን ያደረገው በሚሊኒየም አዳራሽ ሲሆን በምርቃቱም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አምባሳደሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች መገኘታቸው ተገልጿል።
   ከተመራቂዎቹ መካከል 5 ሺህ 295 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 2ሺህ 835 በሁለተኛ ዲግሪ እና 125 ደግሞ በዶክትሬት ዲግሪ የሚመረቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ በስደት የገቡና በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ ተመራቂዎችም ይገኙበታል።

  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ፀጋየ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት 63 ጊዜ እያስመረቀ መሆኑን ጠቁመው፥ በአጠቃላይ ባሉት 13 በላይ ካምፓሶች 50 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።


   ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ በስደት የገቡና ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገድና ለፍሬ በማብቃቱ ረገድ አሁንም ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።



  በምረቃ ስነስርአቱም ላይ ዩኒቨርሲቲው  ለአራት ሰዎች የክብር ዶክትሪት የሰጠ ሲሆን፤ ለጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ለኪነጥበብ ባለሙያው አርቲስት ተስፋዬ አበበ "ፋዘር" ለታሪክ ባለሙያው ፕሮፌሰር አንጀሎ ዴልቦካ፣ እንዲሁም ለአዕምሮ ሀኪሟ ክሌር ፔን የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል


  በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት ለማስቀጠል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምርና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያከናውኑትን ተግባር ማጠናከር እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment