በአብዛኛው የሃገር ውስጥ ጥሬ እቃ በመጠቀም በአንድ ጊዜ ሰድስት ሰዎችን ማጓጓዝ የሚችል ''ሶር ሃይ'' የሚል ስያሜ የተሰጠው ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ በደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቅጅ መሰራቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ከፍሊፒንስ ሞዴል ተቀድቶ በኮሌጁ የተሰራው ይኸው ባጃጅ በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ክልል አቀፍ ኤግዚቪሽንና ባዛር ለእይታ እንደቀረበም በዘገባው ተመልክቷል፡፡
የኮሌጁን ምክትል ዲን አቶ ባሻዬ በየነን ጠቅሶ ዘገባው እንዳመለከተው ባጃጁ በከተሞች የሚስተዋለውን አነስተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ታልሞ የተሰራ ነው፡፡ባጃጁን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከሰባት ወር ያላነሰ ጊዜ የወሰደ ሲሆን የሞተሩን የተወሰነ ክፍል በማሻሻል ሁሉንም ጥሬ እቃ የሃገር ውስጥ ምርት በመጠቀም የተሰራ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።አሁን በገበያ ላይ ያሉት አብዛኞቹ ባጃጆች ሦስት ታሳፋሪዎችን የሚይዙ ሲሆን በቅጅ የተሰራው ባጃጅ ሹፌሩን ሳይጨምር ስድስት ተሳፋሪዎችን በበቂ ሁኔታ በመያዝ በሰዓት እስከ 80 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል በተግባር ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የኮሌጁን ምክትል ዲን በአንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 17 ኪሎ ሜትር ማሽከርከር የሚቻል መሆኑን ጠቁመው፤ ባጃጁ ሙሉ በሙሉ ከፍሊፒንስ ሞዴል የተቀዳ መሆኑን አመልክተዋል። ባጃጁን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 52 ሺህ ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን
አሁን ባልው ገበያም ከ60 ሺህ ብር በላይ መሸጥ ይቻላል፡፡ ከውጭ ሃገራት ከሚመጡት ባጃጆች 30 በመቶ ዋጋ በመቀነስ የሃገር ውስጥ ምርትን ማስፋፋት የሚያስችል እንደሆነም አስታውቀዋል።
No comments:
Post a Comment