የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩት ፖርቱጋላዊው ማሪያኖ ባሬቶን የመረጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያዊውን ውበቱ አባተ ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ የፕሪሜየርሊግ ክለቦችን በማሰልጠን ልምድ ያካበተና አሁንም በሱዳን ሊግ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ጁኔዲን ባሻ ለሱፐር ስፖርት እንደተናገሩት አቶ ውበቱ አባተ የተሾመው የሀገሪቱን አሰልጣኞች ከውጭ ከመጡ አቻዎቻቸው ትምህርት እንዲወስዱ በተያዘው ስትራቴጅክ ፕላን መሰረት የሚመጥን ሆኖ በመገኘቱ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ዉበቱ አባተ በሀገር ውስጥ ሊጎችና በውጭ ያለው ልምድ ለባሪቶም የላቀ ሚና እንደሚጫወት አምነን መርጠነዋል በማለት ተናግረዋል አቶ ጁኔዲን ፡፡ አቶ ጁኔዲን ጨምረውም የምክትል አሰልጣኙ መሾም ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በፍጥነት ወደ ዝግጅት እንዲገባ ይረዳል ብለዋል፡፡በውጭ ሀገር የሚኖሩና ለሀገራቸው መጫወት የሚፈልጉ ብቁ ተጨዋቾች ካሉ በብሔራዊ ቡድኑ የመካተት ዕድል እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችን በመመልመል ዝግጅት ለመጀመር ከተለያዩ ክለቦች አሰልጣኞች ጋር አየተወያዩ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ዘገባው የሱፐር ስፖርት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment