በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ናይጄሪያ ፣ ኬንያ ፣ ግብፅ እንዲሁም ዚምባቡዌየሚገኙ ባለሀብቶችን በዚሁ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።
ኢትዮጵያዊው የሚድሮክ ግሩፕ እና ደርባ ስሚንቶ መስራች ሼክ ሞሃመድ አሊ አላሙዲን በዚህ ዝርዝር ውስጥ በሶስተኝነት ተቀምጠዋል።ሚድሮክ ግሮፕ በዋናነት በወርቅ ማዕድን ፣ በግብርና ፣ በስሚንቶ እና በብረታ ብረት ምርት ላይ በመሰማራት ውጤታማ መሆን እንደቻለ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም በቴሌኮምንኬሽን ዘርፍ የተሰማሩት የሱዳኑ ሞ ኢብራሂም ፣ የ74 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ የንግድ ኢንቨስትመንት ተቋም መስራች አለን ግሬይ ፣ ናይጄሪያዊው የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ደቡብ አፍሪካዊው የቢድቬስት ግሩፕ መስራች በመሆን ለ100, 000 ዜጎች የእንጀራ በር የከፈተው ብራያን ጆፌ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።
No comments:
Post a Comment