
ይሻሻላሉ ተብለው ከተጠበቁ ሶስቱ
የዓለም ክብረ ወሰኖች አንዱ የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ የ2 ሺህ ሜትር ውድድር ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ባይሳካም አትሌቷ የአፍሪካ ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን
ችላለች። ገንዘቤ
በውድድሯ እስከ ግማሽ ርቀት የፈጀባት ሰዓት የዓለምን ክብረ ወሰን ለማሻሻል እንደሚያስችላት ቢገመትም የመጨረሻው 9 መቶ ሜትር
ብቻዋን መሮጧ የዓለምን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ሳትችል ቀርታለች። በመሆኑም አትሌት ገንዘቤ ከ20 ዓመት በፊት በርቀቱ ተያዞን ከነበረው የዓለም ከብረ ወሰን ሰዓት በ2 ሰከንድ ዘግይታ ገብታለች።
ከ20 ዓመት በፊት የ2 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በ5፡25.36 በሆነ ሰዓት
በሶኒያ ሱሊቫን የተያዘ ሲሆን ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን 5፡27.36 በሆነ ሰዓት መግባት ችላለች። ይህም ሰዓት አትሌት ገንዘቤ
ዲባባን በአፍሪካ የርቀቱ አዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል።
No comments:
Post a Comment