የኢትይጵያ አየር መንገድ ከ9 እስከ 15 ወራት ያሰለጠናቸውን 147 የበረራ ባለሞያዎችን አስመረቀ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰልጥኖ ካስመረቃቸው የበረራ ባለሙያዎች ውስጥ 10 የአውሮፕላን አብራሪ ፓይለቶች፣ 92 የአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሻኖች፣ 20 የበረራ አስተናጋጆችና 25ቱ ደግሞ የሽያጭ ባለሞያዎች ናቸው፡፡ አየር መንገዱ ለ159ኛ ጊዜ ሀሙስ ሰኔ 12/2006 ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ ከናይጄሪያ፣ ከየመንና ከሊቢያ የተወጣጡ ተማሪዎችም ይገኙበታል፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በምረቃው ላይ እንዳሉት ላለፉት 4 ዓመታት ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ የአቪዬሽን አካዳሚውን የቅበላ አቅም በአመት 1ሺ ለማድረስ ተችሏል፡፡
አየር መንገዱ በ2025 ለመድረስ ለያዘው ራዕይ በአመት 4ሺ ተማሪዎችን በመቀበል የሀገሪቱን ፍላጎት ብቻም ሳይሆን በአፍሪካም እያደገ የመጣውን የሰለጠነ የበረራ ባለሞያዎች ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቪዬሽን አካዳሚ የ2014 የአመቱ ምርጥ አካዳሚ የሚል እውቅና ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
ምንጭ ፡- ኢ.ሬ.ቴ.ድ
No comments:
Post a Comment