Thursday, June 26, 2014

የጋና ብሔራዊ ቡድን ገንዘብ ካልተከፈለን አንጫወትም አሉ


   የጋና ብሔራዊ ቡድን ገንዘብ ካልተከፈለን የዛሬውን ከፖርቱጋል ጋር የሚኖረንን ወሳኝ ጨዋታ አንጫወትም ማለታቸውን ተከትሎ የአገሪቱ መንግስት $3 ሚሊዮን ዶላር የጫነውን አውሮፖላን ልኮ ገንዘቡ ብራዚል ደርሶ ተጨዋቾቹ ገንዘባቸውን ተከፋፍለዋል።


  በተጨማሪ የጋና የእግር ኳስ ፌደሬሽን ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ቀጣች ቢቢሲ የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ዋቢ አድርጎ እንዳስነበበው ሱሊሙንታሪ እና ቦአቲንግ በስነ ምግባር ግድፈት ምክንያት ከቡድኑ እንዲቀነሱ ሆኗል። ቦአቲንግ አሰልጣኙን ፀያፍ ስድብ ተሳድቧል ሲባል ሱሉሙንታሪ በበኩሉ ሞሰስ አርማህ የተባሉትን ከቡድኑ ኮሚቴ ሀላፊዎች መካከል አንደኛውን አባል ለመምታት ተጋብዟል ይላል።

  ጋና ዛሬ ምሽት 1 ሰአት ላይ ወሳኝ ጨዋታዋን ከፖርቱጋል ጋር ታደርጋለች። የጋና ተጫዋቾች ቀደም ሲል ገንዘብ ካልተሰጠን ይህን ጨዋታ አናደርግም ብለው ነበር ይህን ተከትሎ ፌዴሬሽናቸው እሮብ እለት በቻርተር አውሮፕላን 3 ሚሊየን ዶላር ወደ ስፍራው ልኮ ተጫዋቾቹ እንዲካፈሉት ማድረጉን አሳውቋል።

 በተለይ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ተጫዋቾች ከእንደዚህ አይነት ድርጊት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል። ካሜሮን እና ናይጄሪያ ከነዛ መካከል ነበሩ አሁን ደግሞ ጋና ተደግማለች ። ይህን ምን ይሉታል  ?

No comments:

Post a Comment