በአማራ ክልል ኮምቦልቻ እየተገነባ ያለው ኤርፖርት ከሁለት ወር በኃላ አገልግሎት መስጠት
እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት አስታወቀ። የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድም
ተክሉ እንደገለጹት ኤርፖርቱ በአሁኑ ጊዜ በአስፓልት ደረጃ ተጠናቋል።
ኤርፖርቱ 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት ላለፉት 3 አመታት ግንባታው
ሲካሄድ ቆይቷል። የኤርፖርቱ
ስራ መጀመርም በአገሪቷ ያሉትን ኤርፖርቶች ቁጥር ወደ 18 ያሳድገዋል። የኮምቦልቻ ኤርፖርት ትልልቅ አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም
እንዳለው ሃላፊውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment